አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ሊቨርፑል እና ማንችስተር ዩናይትድ በቫሌንሲያው የ20 አመት ኮከብ ፌራን ቶሬስ ላይ ተፋጠዋል። ቫሌንሲያዎች ከመስመሩ ተጨዋች ከፍተኛ ገንዘብ ማግኘት ይፈልጋሉ።ተጨዋቹ በክረምት መልቀቁ አይቀሬ ሲሆን ጁቬንትስ ፣ ዶርትመንድ እና ማን.ሲቲም ልጁን ለመውሰድ ይፈልጋሉ።
አርሰናሎች ጀርመናዊውን የ31 አመት ተከላካይ ጄኦሬም ቦአቴንግን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው። እንደ ፎት መርካቶ ዘገባ ከሆነ አርሰናል ተጨዋቹን በጥር ለማስፈረም ፈልጎ የነበረ ሲሆን በመጨረሻም ፓብሎ ማሪን ከፍላሚንጎ በውሰት ማስፈረሙ ይታወሳል። አሁን ላይ ግን ቦአቴንግን እንደሚያስፈርሙ ተማምነዋል ቸልሲም የልጁ ፈላጊ ነው።
ቶተንሀሞች አዲሱን ካንቴ እየተባለ የሚጠራውን የአንጀርሱን አማካይ ባፕቲስቴ ሳንታማሪያን ለማስፈረም ትልቅ ተስፋ አድርገዋል። ተጨዋቹ በሌስተር እና ኤቨርተን በጥብቅ ይፈልጋል። የ25 አመቱ ኮከብን ክለቡ በክረምት ለመልቀቅ ዝግጁ ሲሆኑ ልጁም ወደ ፕሪሚየር ሊግ መዘዋወር እንደሚፈልግ ኤክስፕረስ ስፖርት አስነብቧል።
ዌስትሀም ዩናይትዶች እራሳቸውን ከማሪዮ ጎትዜ ዝውውር ላይ አውጥተዋል። እንደ ቢልድ ዘገባ ከሆነ ተጨዋቹ ከፕሪሚየር ሊግ ይልቅ ወደ ጣሊያን ሴሪያ ለማምራት ነው ፍላጎት ያለው።በጣሊያን ክለቦችም እየተፈለገ የሚገኘው ጎትዜ ቀጣይ ማረፊያው ሮማ እንደሚሆን እጅጉን ተገምቷል። እንዲሁም የሚላን ከተማ ክለብ የሆነው ኤሲሚላንም የተጨዋቹ ፈላጊ ነው።
ባርሴሎናዎች አንቱዋን ግሬዝማንን ለመሸጥ ዝግጁ ናቸው። እንደ Sport ዘገባ ከሆነ ባርሴሎናዎች በክረምት የኔይማርን እና የላውታሮ ማርቲኔዝን ዝውውር ለመጨረስ ሲሉ ግሪዝማንን ለመሸጥ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል።የ29 አመቱን ፈረንሳዊ ኮከብ ለማስፈረም ፒኤስጂ እና ማን.ዩናይትድ ተፋጠዋል።
ማንችስተር ሲቲዎች የፋቢያን ሩይዝን ዝውውር ለማሸነፍ ተቃርበዋል።ሲቲዎች የ23 አመቱን አማካይ ለማስፈረም ከባርሴሎና እና ከሪያል ማድሪድ ጋር ፉክክር ቢገጥማቸውም በመጨረሻም ተጨዋቹን ለማስፈረም ተቃርበዋል። ናፖሊዎች ከተጨዋቹ £88m እንደሚፈልጉ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።
ሊቨርፑሎች ሁለት ዝውውሮችን ከአንድ ክለብ ላይ ማጠናቀቅ እንደሚፈልጉ ተሰምቷል። ሊቨርፑሎች ለተጨዋቾቹ እስከ £88m መድበዋል። እንደ ኤክስፕረስ ዘገባ ከሆነ ሊቨርፑል የሚፈልጋቸው ተጨዋቾች የቦሩሲያ ሞንቼግላድባዎቹን የተከላካይ አማካይ ዴኒስ ዛካሪያ እና የመስመር ተጨዋች ማርከስ ቱራምን ነው። ዛካሪያ ከሊቨርፑል በተጨማሪ በማን.ዩናይትድ እና አርሰናልም ይፈለጋል።
No comments:
Post a Comment