Sunday, April 5, 2020

የዕለተ ሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                         አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ


ቶተንሀሞች ከአሁኑ በክረምት ተጨዋቾችን ለማዘዋወር እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ለቶተንሀሞች የተጨናነቀ የዝውውር መስኮት እንደሆነ ሚጠበቀው የክረምቱ የዝውውር ወቅት ከአሁኑ ቶተንሀሞች አምስት ቦታዎች ላይ ተጨዋቾችን ማስፈረም ይፈልጋሉ። ቶተንሀሞች ማስፈረም የሚፈልጓቸው ቦታዎች ይፋ ሲደረጉ የመስመር ተከላካይ ፣ የመሀል ተከላካይ፣ የአጥቂ አማካይ እንዲሁም የፊት መስመር ተጨዋች ነው።





ኒውካትል ዩናይትዶች የሁለቱን ወጣት ወንድማማቾች አማካይ ተጨዋቾችን ኮንትራት ለማራዘም ንግግር ጀምረዋል። ከኒውካስትል ወጣት ቡድን የተገኙት አማካዮቹ በዘንድሮ የኒውካስትል ስብስብ ውስጥ ትልቁን ድርሻ ተወተዋል ተጨዋቾቹ በማንችስተር እና በአርሰናል ይፈለጋሉ።





ሌስተር ሲቲዎች በክረምቱ የዝውውር መስኮት አዲሱ ኒጎሎ ካንቴ እየተባለ የሚገኘውን የአንጀርሱ የተከላካይ አማካይ ባፕቲስቴ ሳንታማሪያ ለማስፈረም ተቃርበዋል። ሌስተሮች በተደጋጋሚ መልማዮችን በመላክ ልጁን ተመልክተውታል።ተጨዋቹን ከሌስተር በተጨማሪ ቶተንሀም እና ኤቨርተን ይፈልጉታል።





ዩናይትዶች ፊሊፔ ኩቲንሆን ለማስፈረም የተሻለ ዕድል አላቸው ተብሏል።በጥሩ የዝውውር መስኮት ብሩኖ ፈርናንዴዝን ያመጡት ቀያዮቹ ሰይጣኖች በቀጣይ ብራዚላዊውን የአጥቂ አማካኝ ለመጨመር አስበዋል።





ቸልሲዎች የጃደን ሳንቾን ዝውውር በመተው ሙሉ በሙሉ ፊታቸውን ወደ ፊሊፔ ኩቲንሆ አዙረዋል። እንደ Sport ዘገባ ከሆነ ሳንቾ አሁን ላይ ዩናይትድን መምረጡ እውን መሆኑን ተከትሎ ቸልሲዎች ፊታቸውን ወደ ኩቲንሆ እንዲያዞሩ አስገድዷቸዋል ይላል መረጃው።





ቶተንሀሞች ከሀሪ ኬን ዝውውር እስከ £150m ይፈልጋሉ።ከሰሙኑ በክረምት ቶተንሀምን እንደሚለቅ በሰፊው እየተነገረ ይገኛል። ተጨዋቹን የተለያዩ ክለቦች ይፈልጉታል አሁን ላይ ግን ማንችስተር ሲቲ እና ሪያል ማድሪድ የልጁ ዋነኛ ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል።






እንደ ስፔኑ ማርካ ጋዜጣ አሁንም ሪያል ማድሪዶች የፖል ፖግባ ፈላጊ ናቸው።ፖግባ ስሙ አሁን ላይ ከጁቬንቱስ ጋር ቢነሳም ማድሪዶች ግን ልጁን በክረምት በርናባው ለመውሰድ እንደሚሰሩ ጋዜጣው አስነብቧል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...