Sunday, April 5, 2020

የዕለተ እሁድ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

                  አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ



ዩናይትዶች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ሶስት ትላልቅ ዝውውሮችን ለመጨረስ እንቅስቃሴዎችን ጀምረዋል። እንደ M.E.N ዘገባ ከሆነ ዩናይትዶች በክረምቱ ሊፈፅሟቸው ያሰቡዋቸው ዝውውሮች የቶተንሀሙን ሀሪ ኬን ፣ የዶርትመንዱን ሳንቾን እንዲሁም የጁቬንቱሱን ማቲያስ ዴላይት እንደሆኑ ጋዜጣው አስነብቧል።





ያለፉት ቀናት የኢንተር ሚላን ተጨዋቾች በተጋጋሚ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ስማቸው ሲያያዝ ሰንብቷል። ሲቲዎች ላውታሮ ልቡ ወደ ባርሴሎና ስለሸፈተ እሱን በመተው ሌሎቹን ሁለት ተጨዋቾችን ግን ለማስፈረም በክረምት የዝውውር መስኮት እንደሚፈልጉ ይፋ ተደርጓል። እንደ ሜይል ዘገባ ከሆነ ሲቲዎች ሊያስፈርሟቸው ሚፈልጉት ስክሪነር እና ባስቶኒን ነው።






ናፖሊዎች በክረምት ከቸልሲ መልቀቁ እውን እየሆነ የመጣውን የግራ መስመር ተከላካይ ኤመርሰን ፓልሜራስን በክረምት ለማስፈረም ለተጨዋቹ ኮንትራት መስጠታቸው ተሰምቷል። እንደ
ቱቶ ስፖርት ዘገባ ናፖሊዎች ለተጨዋቹ የአምስት አመት ኮንትራት እና አመታዊ የ£3m ክፍያን አቅርበውለታል።






የኤቨርተኑ አማካይ በርናርድ በክረምት ኤቨርተንን መልቀቅ እንደሚፈልግ እና ወደ ጣልያኑ ሮማ ለማቅናት እንደሚፈልግ ተሰምቷል። ኤቨርተኖች ከተጨዋቹ £16m የሚፈልጉ ሲሆን በርናርድ ወደ ሮማ ሚያቀና ከሆነ ከቀድሞ አሰልጣኙ ፎንሴካ ጋር በድጋሚ የሚሰራ ይሆናል።





ጁቬንቱሶች ጋብርኤል ጄሰስን ለማግኘት ዳግላስ ኮስታን የዝውውሩ አካል ለማድረግ አስበዋል። እንደ ካልቺዮ መርካቶ ዘገባ ጁቬዎች የ29 አመቱን ኮስታን በቱሪን ማቆየት አይፈልጉም።ይህን ተከትሎ ዝውውሩን እንደ አማራጭ ይዘውታል።





የኢቫን ራኪቲች ቆይታ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ገብቷል።በ2014 ከሲቪያ አስፈርመውት ለባርሴሎና 299 ጨዋታዎችን ማድረግ የቻለው ራኪቲች ኮንትራቱ 2021 የሚጠናቀቅ ሲሆን ባርሳዎች እሱን ላለማጣት እስከ £17m ለመሸጥ ይፈልጋሉ።ማንችስተር ዩናይትድ የልጁ ዋነኛ ፈላጊ ሲሆን አሁን ላይ ደግሞ አትሌቲኮ ማድሪድ ራኪቲችን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይቷል።





ፈረንሳዊው የሪያል ማድሪድ ተከላካይ ራፋኤል ቫራን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከማድሪድ መውጣት እንደማይፈልግ ዴይሊ ስታር አስነብቧል። ፔፕ የ26 አመቱን ፈረንሳዊ ለማስፈረም ቢፈልግም ተጨዋቹ ግን ምርጫው ቤርናቦ ሆኗል።





አርሰናሎች  በሄነሪክ ሚኪታሪያን ዝውውር ላይ ለሁለተኛ ጊዜ የሮማን ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል ሮማዎች የተጨዋቹን ውል ቋሚ ለማድረግ ለአርሰናል £10m ለመክፈል ሲፈልጉ አርሰናሎች ደግሞ ከተጨዋቹ £18m እንደሚፈልጉ  ነግረዋቸዋል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...