አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ

ማንችስተር ዩናይትዶች ለሳኡል ኒግዌዝ £132m ለመክፈል ፍቃደኛ አይደሉም። ከሰሞኑ እንደወጡ መረጃዎች ከሆነ ዩናይትዶች በክረምት ፖግባን ለቀው ኒግዌዝን ከአትሌቲኮ ማድሪድ ለማስፈረም እንደሚፈልጉ መሰማቱ ይታወሳል ፥ አትሌቲኮዎችም ማንኛውም የኒግዌዝ ፈላጊ ክለብ ተጨዋቹን ለመውሰድ £132m ማቅረብ እንዳለበት መናገራቸው ይታወሳል ፥ ነገር ግን ዩናይትዶች ለተጨዋቹ ከ£70m በላይ ማቅረብ አይፈልጉም።
ባየርን ሙኒኮች የጊዜያዊውን አሰልጣኝ ሀንስ ፍሊክን ተጨማሪ ኮንትራት ሰተውታል።ሙኒኮች አሰልጣኙን ፍሊክን እስከ 2023 የሚያቆየውን ውል ነው ያስፈረሙት።
ማንችስተር ሲቲዎች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከተሳካላቸው ከኢንተር ሚላን ሶስት ተጨዋቾችን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።የመጀመሪያ ምርጫቸው ወደ ባርሴሎና ሊያቀና የተቃረበው ማርቲኔዝ ሲሆን በተጨማሪም አሌሳንድሮ ባስቶኒ እና ሚላን ስክሪነር ናቸው።
ባርሴሎናዎች ብራዚላዊው አማካይ ፊሊፔ ኩቲትሆ ላይ የመሸጫ ዋጋ ለጥፈውበታል።ባርሴሎናዎች ኩቲንሆን ፈልጎ ለሚመጣ ማንኛውም ክለብ ከ£70m-£79m እንደሚፈልጉ ይፋ አድርገዋል።ተጨዋቹ በእንግሊዞቹ ክለቦች በጥብቅ እንደሚፈለግ ይታወሳል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውሳኔ
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የበላይ አስተዳዳሪዎች ባደረጉት ስብሰባ መሰረት ሊጉ አስቀድሞ በተያዘለት ቀን እንደማይካሄድ አስታውቀዋል።የእንግሊዝ ውድድሮች ለማካሄድ አመቺ ሁኔታዎች ከሌሉ በቀር እንደማይካሄድም ይፋ አድርገዋል።
ኤቨርተኖች ሁለቱን የሪያል ማድሪድ ኮከቦች ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው።እንደ ማርካ ዘገባ ከሆነ ኤቨርተኖች በዚዳን ስር ቦታ የሌላቸውን ሀሜስ ሮድሪጌዝን እና ጋሪዝ ቤልን በክረምት ለማስፈረም ዝግጁ ናቸው።ነገር ግን ኤቨርተኖች የቤልን ሳምንታዊ ደሞዝ የመክፈል አቅም ላይኖራቸው እንደሚችል ማርካ አያይዞ ዘግቧል።
ጁቬንቱሶች ሮናልዶን እና ሂግዌንን ለመተካት የተለያዩ አጥቂዎችን እየተመለከተ ይገኛሉ።እንደ ቱቶ ስፖርት ዘገባ ከሆነ ጁቬንቱሶች በድጋሚ አይናቸውን ወደ ብራዚላዊው አጥቂ ጋብርኤል ጄሰስ አዙረዋል።ሲቲዎች ተጨዋቹን የረጅም ጊዜ የአጉዌሮ ተተኪ አድርገው ስላሰቡት በቀላሉ እንደማይለቁት ይጠበቃል።
አርሰናል እና ቸልሲ በፈረንሳዊው የባርሴሎና ተከላካይ ሳሙኤል ኡምቲቲ ላይ ፍላጎት አሳይተዋል። ባርሴሎናዎች ከተጨዋቹ እስከ £36m ይፈልጋሉ።እንደ ኤክስፕረስ ዘገባ ከሆነ ሁለቱ ክለቦች ለተጨዋቹ እስከ £25m ለመክፈል ይፈልጋሉ።
good
ReplyDeleteThanks in your information
ReplyDelete