Friday, April 3, 2020

የዕለተ አርብ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                   አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ



ዩናይትዶች የቶማስ ሙንየር ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል። በፓርክ ደ ፕሪንስ ኮንትራቱ ክረምት ላይ የሚያበቃው ሙንየርን ለማስፈረም ሶልሻየር እጅጉን ይፈልጋሉ።ከዩናይትድ በተጨማሪ ተጨዋቹን በነፃ ለማስፈረም ቶተንሀም ፣ ቦ.ዶርትመንድ እና ኤሲ ሚላን ይፈልጋሉ።





ጁቬንቱሶች በክረምት ኮንትራቱ ከቸልሲ ጋር የሚጠናቀቀውን ዊሊያንን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል።ጁቬዎችም ከወኪሉ ጋር ንግግር ለማድረግ ዝግጁ ናቸው። የቀድሞ የቸልሲ አሰልጣኝ ማውሪዚዮ ሳሪ ልጁ ወደ ጁቬ እንዲመጣላቸው እንደሚፈልጉ ቱቶ ስፖርት አስነብቧል።በተጨማሪም ጆዜ ወደ ቶተንሀም እንዲመጣላቸው ይፈልጋሉ።





እንደ ሜይል ዘገባ ከሆነ ዌስትሀም ዩናይትዶች በክረምት የባርሴሎናውን አጥቂ ብራይት ዋይትን ማስፈረም ይፈልጋሉ። ተጨዋቹ ባርሴሎና በክረምት ማርቲኔዝን እና ኔይማርን ለማስፈረም ማሰቡን ተከትሎ ቡድኑን ለመልቀቅ ዝግጁ ሲሆን ባርሴሎና ከተጨዋቹ እስከ £15m ይፈልጋል።





ክሮሺያዊው የ31 አመት አማካይ ኢቫን ራኪቲች በክረምት ባርሴሎናን ለመልቀቅ ዝግጁ ሆኗል። በባርሴሎና ቤት የመሰለፍ እድልን እያገኘ የሚገኘው ራኪቲች ኮንትራቱ በ2021 የሚጠናቀቅ ሲሆን ባርሴሎናዎች ተጨዋቹን በነፃ በቀጣይ አመት ላለመልቀቅ ሲሉ በክረምት እስከ £18m ለሚያቀርብ ክለብ ለመሸጥ ዝግጁ ሆነዋል።






ከቱርኩ ትራብዞንስፖር ከተለያየ በኋላ ክለብ አልባ ሆኖ የቀረው የቀድሞ የቸልሲ አማካይ ጆን ኦቢ ሚኬሌ አዲስ ክለብ ለማግኘት ተቃርቧል። እንደ ያሆ ስፖርት ዘገባ ከሆነ ሚኬሌ ከብራዚሉ ቦታፎጎ ጋር ግንኙነት የጀመረ ሲሆን ዝውውሩ በዚህ ሳምንት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።





አርሰናሎች ዳኒ ሴባዮስን በክረምት ወደ ማድሪድ በመሸኘት በሱ ቦታ ሌላ አማካይ ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው። እንደ Sport ዘገባ ከሆነ አርሰናሎች የሚፈልጉት ተጨዋች የኢስፓኞሉ የ23 አመቱ ማርክ ሮካ ነው።አርሰናሎች ለተጨዋቹ እስከ £35m ያስወጣቸዋል ፥ ተጨዋቹ በባየርን ሙኒክ እና በኢንተር ሚላን ይፈለጋል።





ቸልሲዎች አራት ተጨዋቾችን በክረምት በመልቀቅ ሁለት ተጨዋቾችን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።እንደ Football.London ዘገባ ከሆነ ቸልሲዎች ሁለቱን የመስመር ተከላካዮች አሎንሶን እና ኤመርሰንን እንዲሁም አማካዩን ባርክሌይን እና አጥቂውን ባትሹዋይን በመሸጥ እስከ £100m ማግኘት ይፈልጋሉ።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...