አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ፈረንሳዊው ኦሊቨር ዡሩድ በክረምት ስታንፎርድ ብሪጅን መልቀቁ አይቀሬ እየሆነ ነው። እንደ ቱቶ ስፖርት ዘገባ ከሆነ ዡሩድ ተጨማሪ የአንድ አመት ኮንትራት የቀረበለት ቢሆንም ጥያቄውን ውድቅ አድርጎ ወደ ኢንተር ሚላን ለማምራት ዝግጁ ሆኗል።
በ2014 ከስፖቲንግ ሊዝበን በ16ሚ.ፓ ዩናይትድን የተቀላቀለው ማርኮስ ሮኾ ይሄ አመት በዩናይትድ የመጨረሻው እንደሆነ ተሰምቷል።ባለፉት ሶስት አመታት በፕሪሚየር ሊጉ 17 ጨዋታ ብቻ ለዩናይትድ ያደረገው ሮኾ በክረምቱ ዩናይትድን ለመልቀቅ ዝግጁ ነው። እንደ ጋዜጣ ዴሎ ስፖርት ዘገባ ከሆነ ሮማዎች የተጨዋቹ ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል።
አርሰናሎች በክረምቱ ከኮንትራት ነፃ የሚሆነውን የፒኤስጂውን ላይቪን ኮሩዙዋን ለማስፈረም ይፈልጋሉ። ከተጨዋቹ ወኪል ጋርም ለመነጋገር ዝግጁ ናቸው። ነገር ግን የስፔኑ Sport ጋዜጣ እንዳስነበበው ከሆነ አርሰናሎች ተጨዋቹን ለማግኘት ከሊቨርፑል ፣ ባርሴሎና ፣ ናፖሊ እና ኢንተር ሚላን ፉክክር እንደገጠማቸው ታውቋል።
ዜናው ብዙም ባይጠበቅም ሌስተር ሲቲዎች አዲሱ የፊሊፔ ኩቲንሆ ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል። ባርሴሎናዎች በክረምት ኔይማርን እና ማርቲኔዝን ለማስፈረም ስላቀዱ ተጨዋቾችን ለመልቀቅ ዝግጁ ናቸው። ከነሱ ውስጥም ኩቲንሆ የመጀመሪያው ነው። እንደዘገባው ከሆነ ሌስተሮች የልጁ ዋነኛ ፈላጊ ሆነዋል።ተጨዋቹ በቶተንሀም ፣ በቸልሲ እና በዩናይትድም ይፈለጋል።
ማንችስተር ዩናይትዶች በድጋሚ የማቲያስ ዴላይት ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል።እንደ ጣሊያኑ ካልቺዮ መርካቶ ዘገባ ከሆነ ዩናይትዶች ፖግባን በማትያስ ዲላይት የመቀየር ሀሳብ ሊያቀርቡ ነው።ዩናይትዶች በዚህ ሳምንት ከሁለቱም ወኪል ሚኖ ራዮላ ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ ይዘዋል።
ቦ.ዶርትመንድ በዩናይትድ በጥብቅ ሚፈለገውን የበርኒንግሀሙን የ16 አመት ኮከብ ቤሊንግሀምን ለማስፈረም ተቃርበዋል። እንደ ዴይሊ ሜይል ዘገባ ከሆነ ዶርትመንዶች ተጨዋቹን ሚያስፈርሙ ከሆነ ሳንቾን ለመልቀቅ እንደሚፈልጉ ተሰምቷል።
ሀሜስ ሮድሪጌዝ በክረምት ከበርናባው መልቀቅ እንደሚፈልግ እና ከቀድሞ አለቃው ጋር በድጋሚ መስራት እንደሚፈልግ ተሰምቷል። ተጨዋቹን ኤቨርተን እንደሚፈልገው በተደጋጋሚ ተነግሯል። ሀሜስም ከሌሎች ክለቦች ኤቨርተንን እንደመረጠ የመርሲሳይድ ጋዜጣ አስነብቧል።
No comments:
Post a Comment