Wednesday, April 1, 2020

የዕለተ ረቡዕ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                  አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ


ቸልሲዎች ማኑዬል ኑዌርን ለማስፈረም እጅጉን ፍላጎት አሳይተዋል።በሙኒክ ኮንትራቱን ለማራዘም ፍቃደኛ ያልኾነው ኑዌር በክረምት ክለቡን መልቀቅ ይፈልጋል።ተጨዋቹ ደሞ በቸልሲዎች እጅጉን ይፈለጋል።





አርሰናሎች አይናቸውን ወደ ሪያል ማድሪድ ኮከቦች ላይ አድርገዋል። ተጨዋቾቹም ሀሜስ ሮድሪጌዝ እና ሉካ ዮቪች ናቸው። አርሰናሎች የሀሜስ ዝውውር ላይ ከቀድሞ የሀሜስ አለቃው የአንቾሎቲው ኤቨርተን ከባድ ፈተና ሲጠብቃቸው በሉካ ዮቪች ዝውውር ደሞ ከከተማ ክለባቸው ቶተንሀም ከባድ ፉክክር ይጠብቃቸዋል።





ሊቨርፑሎች በድጋሚ ራሂም ስተርሊንግን ወደ አንፊልድ ለመመለስ ፍላጎት አላቸው። በ2015 ወደ ሲቲ ካመራ በኋላ በተደጋጋሚ የሊቨርፑል ደጋፊ እንደሆነ ሲናገር የሰነበተው ስተርሊንግ ሊቨርፑሎች ሳዲዮ ማኔን በክረምት ሚለቁት ከሆነ የመጀመሪያ ምርጫቸው ስተርሊንግ እንደሆነ ሌኪፕ አስነብቧል።





ማንችስተር ዩናይትዶች የመስመር ተከላካይ ለማስፈረም አይናቸውን ወደ ናፖሊው ጆቫኒ ዲሎሬንዞ አዙረዋል።ተጨዋቹ በ2019 ነበር ናፖሊን በ£7m ከኢምፖሊ የተቀላቀለው። ተጨዋቹ በናፖሊ 35 ጨዋታ አድርጎ 2ጎል እና 7ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ማቀበል ችሏል።





ኤቨርተኖች የሊሉን ተከላካይ ዝውውር ለማሸነፍ ተቃርበዋል።በአርሰናል በቸልሲ ሲፈለግ የነበረውን የ22 አመቱን ጋብርኤል ማግላሀስን ዝውውር ሊጨርሱ ከጫፍ ደርሰዋል።ኤቨርተኖች ለተጨዋቹ £30m ለመክፈል ዝግጁ ናቸው።





ቦሩሲያ ዶርትመንዶች በትልልቅ የአውሮፓ ክለብ አይን ውስጥ የገባው ጃደን ሳንቾን የመሸጫ ዋጋ ይፋ አድርገዋል።እንደ ስካይ ስፖርት ዘገባ ከሆነ ዶርትመንዶች ከተጨዋቹ £120m ይፈልጋሉ።





ከሪያል ማድሪድ አርሰናልን በውሰት ተቀላቅሎ ብዙም የተሳካ አመትን ያላሳለፈው ስፔናዊው ዳኒ ሴባዮስ በክረምት አርሰናልን መልቀቅ እንደሚፈልግ ተሰምቷል።የተጨዋቹም ቀጣይ ማረፊያ ሪያል ቤትስ ሊሆን ይችላል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...