አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ሪያል ማድሪዶች አሁንም ፊታቸውን ወደ ብራዚላዊው የሳኦ ፓውሎ የ21 አመት ኢጎር ጎሜዝ አዙረዋል። ተጨዋቹ በትላልቅ የአውሮፓ ክለቦች የሚፈለግ ሲሆን ማድሪዶች ከሌሎች ክለቦች በመቅደም ሊያስፈርሙት እንቅስቃሴ ጀምረዋል። እንደ As ዘገባ ከሆነ ተጨዋቹ በባርሴሎና ፣ በሲቪያ እና በአያክስ ይፈለጋል።
ዝውውሩ እውነት መሆኑ እርግጥ ባይሆንም ዩናይትድ ጃደን ሳንቾን ለማስፈረም ከስምምነት መድረሱ ተሰምቷል። ዩናይትዶች ለተጨዋቹ £120m ለመክፈል ሲስማሙ ለተጨዋቹም ሳምንታዊ 400.000ሺፓ ይከፍላሉ ፥ በዩናይትድም 7 ቁጥርን እንደሚለብስ ተሰምቷል።
ቸልሲ እና ቶተንሀም በበርንሌው ግብ ጠባቂ ኒክ ፖፕ ላይ ተፋጠዋል። ቸልሲ በክረምቱ ኬፓን ለመልቀቅ ዝግጁ መሆናቸውን ተከትሎ ልጁን ወደ ብሪጅ ለመውሰድ ፍላጎት አላቸው። ቶተንሀምም ቢሆን በሁጎ ሎሬስ ላይ ያላቸው እምነት በመቀነሱ ፖፕን በማስፈረም የሎሬስ ተፎካካሪ ማድረግ ይፈልጋሉ።
የኒሱ ተከላካይ ማላንግ ሳር በተለያዩ የአውሮፓ ክለቦች አይን ውስጥ ገብቷ። ናፖሊዎች በክረምት ኩሊባሊን ሚለቁ ከሆነ ተጨዋቹን እንደሚያስፈርሙት ተማምነዋል። ከናፖሊ በተጨማሪ በቦሩሲያ ሞንቼግላድባ፣ በወልቭስበርግ እንዲሁም በአርቢ ላይብዢክ ይፈለጋል። ተጨዋቹ በኒስ የ12 ወራት ኮንትራት ብቻ ነው ሚቀረው።
ቫሌንሲያዎች ካርሎስ ሶሌር ላይ ዋጋ ለጥፈውበታል።ተጨዋቹን ሚፈልግ ክለብ እስከ £36m መክፈል እንዳለበት ይፋ አድርገዋል። ተጨዋቹ በአርሰናል በጥብቅ ይፈለጋል፥ የአርቴታም ቀዳሚ ተመራጭ ነው።ተጨዋቹ በዩናይትድ፣ በባርሴሎና እንዲሁም በሪያል ማድሪድ ይፈለጋል።
ሊድስ ዩናይትዶች የሜትዙ ኮከብ ዲያሎ ዝውውር ላይ እጃቸውን አስገብተዋል። ተጨዋቹ በቸልሲ በጥብቅ የሚፈለግ ቢሆንም ሊድሶች ለቀጣይ አመት ፕሪሚየር ሊጉን ከተቀላቀሉ ቀዳሚ ፈራሚያቸው ለማድረግ እየሰሩ ነው ፥ ልጁ በክርስቲያል ፓላስም ይፈለጋል።
No comments:
Post a Comment