አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ኦሌ ጉናር ሶልሻየር በቀጣዩ ሳምንት ፖግባ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ የተናገረ ሲሆን ፈረንሳዊው አማካይ ከፈርናንዴዝ ጋር የመሀል ሜዳው ላይ እንደሚጣመርም ይጠበቃል።
ብዙዎች እንደሚስማሙት ብሩኖ ፈርናንዴዝ ቀያይ ሰይጣኖቹን ከተቀላቀለ አንስቶ ትልቅ ለውጥ መፍጠር ችሏል።አሁን ደግሞ የፖግባን ከጉዳት ማገገም ተከትሎ ሶልሻየር ሁለቱንም እንደሚጠቀም ተናግሯል።
ምን አይነት አሰላለፍ ሊኖር ይችላል?
(1) 4-3-3
ብዙዎች የሚጠብቁት በ4-3-3 ዩናይትድ ሊጫወት እንደሚችል ነው።በዚሁም ከሁለቱ ፈጣሪ አማካዎች ጀርባ ፍሬድ ፣ ኒማኒያ ማቲች አሊያም ማክቶሚናይ ሊሰለፉ ይችላሉ።
(2) 4-2-3-1
በዚህ አሰላለፍ ደግሞ ፖግባ በጥልቀት ወደ ኋላ ተስቦ ፥ ፈርናንዴዝ ደግሞ በፈጣሪነት በአስር ቁጥር ሚና ከአጥቂዎች ጀርባ ሊሰለፍ ይችላል።
(3) 3-5-2
ይህ አሰላለፍ ብዙ ጊዜ ዩናይትድ ከቶፕ 6 ክለቦች ጋር የሚጠቀመው አሰላለፍ ሲሆን ዋን ቢሳካ እና ብሬንደን ዊልያምስ የሁለቱን ክንፎች ሲጠቀሙ ሉኬ ሾው ደግሞ ወደ ኋላ ተስቦ ይከላከላል።
በዚህ አሰላለፍ መሰረት መሀል ላይ ፈርናንዴዝ እና ፖግባ ከ ማቲች ጋር ሊጣመሩ ይችላሉ።
(4) 4-1-2-1-2
በዞህ አሰላለፍ ደግሞ ማቲች በተከላካይ አማካይነት ሲሰለፍ ፖግባ ከፍሬድ አሊያም ማክቶሚናይ ጋር ከፊት ተጣምሮ ፈርናንዴዝ ደግሞ በአስር ቁጥር ሚና ሊሰለፍ ይችላል።
(5) 4-1-4-1
በመጨረሻ ሶልሻየር ፔፕ ጋርዲዮላ የሚወደውን እና በባየርን ሙኒክ በብዛት የተጠቀመበትን አሰላለፍ ሊከተል ይችላል።
በዚህ አሰላለፍ ማቲች ከኋላ ደጀን ይሆንና ከፊት ያሉት አራት ተጨዋቾች ላይ በክንፍ ጄምስ እና ራሽፎርድ ሲሰለፉ መሀሉ ላይ ደግሞ ፈርናንዴዝ እና ፖግባ ይሰለፋሉ።
የቱ የተሻለ ይመስልዎታል ? ሐሳብ ይስጡ
No comments:
Post a Comment