አሮጊቶቹ የቶተንሀሙን ኮከብ ሀሪ ኬንን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።ጁቬዎች በቅርብ ሳምንታት ከቶተንሀም ለመልቀቅ ምልክት ያሳየውን ኬንን ማስፈረማቸው አይቀሬ ሆኗል።
ማን ሲቲዎች የኢንተርሚላኑን ወጣት ኮከብ ተከላካይ አሌክሳንደር ባስቶኒን ለማስፈረም ይፈልጋሉ። ፔፕም ልጁን ለማግኘት ካሁኑ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የበላይ ሀላፊዎች ከዚ ሳምንት ጀምሮ ሁሉም የእንግሊዝ ውድድሮች በዝግ ስታድየም እንዲካሄዱ ዛሬ ከሰአት ውሳኔ አስተላልፏል።
የሰሜን ለንደን ክለቦች የሆኑት ቶተንሀም እና አርሰናል የናፖሊውን አጥቂ አርካዲዝ ሚሊክን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል።የኔፕልሱ ክለብ ከተጨዋቹ £40m ይፈልጋል።
በክረምት ከሊዮን ሳይታሰብ ሪያል ቤትስን የተቀላቀለው ናቢል ፈኪር በሎስ ብላንኮሶች የዝውውር ራዳር ውስጥ ገብቷል።
የስፔን ላሊጋ አስተዳደር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የስፔን ላሊጋን ለሁለት ሳምንታት እንዲቋረጥ ከውሳኔ ደርሷል።
አትሌቲኮ ማድሪድ ለረጅም ጊዜ የሚፈልገውን አሌክሳንደር ላካዜትን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከምንግዜውም በላይ ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው።
No comments:
Post a Comment