Friday, March 13, 2020

የዕለተ አርብ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

            አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


አርሰናል በክረምቱ የዝውውር መስኮት የአትሌቲኮ ማድሪዱን አማካይ ቶማስ ፓርቲ ለማዘዋወር ይፈልጋል።ጋናዊውን ኢንተርናሽናል የውል ማፍረሻው £45ሚ. ነው።
(Telegraph)






ጁቬንትስ ፣ አርሰናል እና ቶተንሃም ብራዚላዊውን የጨዋታ ቀማሪ ዊልያን ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።የ30 አመቱ ተጨዋች ግን ለለንደን ክለቦች መጫወትን ነው የሚሻው።
(Tuttosport via Sport Witness)





የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል።በዚህም ምክንያት አርሰናል ቀጣይ ሁለት ጨዋታዎቹ እንዲራዘሙለት ጥያቄ አቅርቧል።
(Mirror)





የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ተጨዋቾቻቸውን ለኢንተርናሽናል ብሬክ መልቀቅ አይፈልጉም።ከወደ ስፔን በወጣ መረጃ ደግሞ ሪያል ማድሪድ ሙሉ ተጨዋቾቹን ኳረንቲን ውስጥ አስገብቷል።
(Mail)





የማንቸስተር ዩናይትዱ አለቃ ኦሌ ጉናር ሶልሻየር የኦዲዮን ኤግሃሎን ውል ቋሚ ለማድረግ እንደሚሰሩ ተናግሯል።ናይጄሪያዊው አጥቂ በውሰት ከሻንጋይ ሺኖዋ ማንቸስተር ዩናይትድን ከተቀላቀለ አንስቶ በስምንት ጨዋታዎች አራት ግብ ማስቆጠር ችሏል።
(Manchester Evening News)





ወደ ቼልሲ መዘዋወሩ ከወር በፊት ይፋ የሆነው ሞሮኳዊው የመስመር አጥቂ ሀኪም ዚያች የአያክሱን ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና ቼልሲን እንዲቀላቀል በማባባል ላይ ነው።
(Mail)




ማንቸስተር ዩናይትዶች ጄደን ሳንቾን ማዘዋወር እንደሚችሉ ተማምነዋል።አምስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ዩናይትድ የማንቸስተር ሲቲን ለሁለት አመት ከሻምፒዮንስ ሊግ መታገድ ተከትሎ ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ የመመለስ ዕድሉ ለቀጣይ አመት ሰፊ ነው።ይህ ደግሞ ተጨዋቹን ለማዘዋወር ጥሩ ዕድል ይሰጣቸዋል።
(Mirror)





ማን ሲቲዎች የኢንተርሚላኑን ወጣት ኮከብ ተከላካይ አሌክሳንደር ባስቶኒን ለማስፈረም ይፈልጋሉ። ፔፕም ልጁን ለማግኘት ካሁኑ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።





የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የበላይ ሀላፊዎች ከዚ ሳምንት ጀምሮ ሁሉም የእንግሊዝ ውድድሮች በዝግ ስታድየም እንዲካሄዱ ትናንት ከሰአት ውሳኔ አስተላልፏል።





No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...