አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ምንም እንኳን አንዳንድ መረጃዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሊቨርፑል የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ዘንድሮ ላይረከብ ይችላል ቢሉም ቴሌግራፍ ግን ዘንድሮ እንደሚረከብ ተናግሯል።
(Telegraph)
ባርሴሎና አርጀንቲናዊውን አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ ከኢንተር ሚላን ለማዘዋወር እየኳተነ ይገኛል።ዛሬ በወጣ መረጃ ደግሞ የካታላኑ ክለብ ለ22 አመቱ አጥቂ £16ሚ. አመታዊ ደሞዝ አቅርቦለታል።
(Star)
ጁቬንትስ ባለፈው የጥር ወር የዝውውር መስኮት ሊያዘዋውረው ሞክሮ ያልተሳካለትን የቼልሲውን ተከላካይ ኤመርሰን ፓልሜሪ በመጪው ክረምት የማዘዋወር እቅድ አለው።አሮጊቷ ለጣሊያናዊው ፉል ባክ £25ሚ. አሰናድታለች።
(Express)
ላዚዮ የቼልሲውን አጥቂ ኦሊቪየር ዢሩ እና የኤሲ ሚላኑን አማካይ ጂያኮሞ ቤናቬንቹራ በአመቱ መጨረሻ በክለባቸው ያላቸው ኮንትራት ሲያበቃ ለማዘዋወር ይፈልጋል።
(Gazzetta dello Sport - in Italian)
ሁለቱ የስፔን ሐያላን ክለቦች ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ ፈረንሳዊውን የሊዮ የ16 አመት አጥቂ ራያን ቼርኪ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።
(Calciomercato - in Italian)
ፓሪሰን ዤርመን አልጄሪያዊውን የማን ሲቲ ተጨዋች ሪያድ ማህሬዝ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።ማህሬዝ በኤቲሀድ እስከ 2023 ማን ሲቲ ከሻምፒዮንስ ሊግ መታገዱ ክለቡን እንዲለቅ ይገፋፋዋል።
(Calciomercato)
የፊዮረንቲናው የመስመር አጥቂ ፌዴሪኮ ቼዛ በፓሪሰን ዤርመን ፣ ኢንተር ሚላን ፣ ጁቬንትስ እና ማንቸስተር ዩናይትድ እየተፈለገ ይገኛል።ቼዜ በዘንድሮው አመት በሁሉም የውድድር አይነቶች ሰባት ግብ ያስቆጠረ ሲሆን ሶስት ኳስም ለግብ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
(Le10Sport)
ኦሌ ጉናር ሶልሻየር ፖል ፖግባ በቀጣዩ አመት በማንቸስተር ዩናይትድ እንደሚቆይ መናገሩን ተከትሎ ጁቬንትስ ሌላ አማራጭ በመፈለግ ላይ ይገኛል።ዋነኛው እቅዱ ደግሞ የሊዮኑ ሀውሳም አውራ ሆኗል።
(Calciomercato)
No comments:
Post a Comment