Thursday, March 12, 2020

የዕለተ ሐሙስ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                   አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ትናንት ምሽት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች የተደረጉ ሲሆን ወደ ሩብ ፍጻሜ ያለፉት ሁለት ክለቦችም ታውቀዋል።በአንፊልድ አትሌቲኮ ማድሪድን ያስተናገደው ሊቨርፑል ባልተጠበቀ ሁኔታ በተጨማሪ ሰዓት 3ለ2 ተሸንፏል።በዚህም አትሌቲኮ ማድሪድ በአጠቃላይ በሁለቱም ጨዋታዎች ሊቨርፑልን በድምር 4ለ2 ረትቶ ወደ ሩብ ፍጻሜው ማለፉን አረጋግጧል።ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት ባለ ድሉ ዲዬጎ ሲሞኒ ሊቨርፑልን "በአሰልጣኝነት ህይወቴ በተቃራኒነት የገጠምኩት ቁጥር አንድ ምርጥ ቡድን" ሲሉ ገልጸውታል።





በሌላ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ፓርክ ደ ፕሪንስ ላይ በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ያለ ደጋፊ ቦሩሲያ ዶርትሙንድን ያስተናገደው ፔዤ 2ለ0 በመርታት ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።ፔዤ በድምሩ 3ለ2 በሆነ ጠባብ ውጤት ነው ቢጫ ሰርጓጆቹን ማሸነፍ የቻለው።





ሁለቱ የማንቸስተር ከተማ ክለቦች ማንቸስተር ዩናይትድ እና ማንቸስተር ሲቲ የቶተንሃሙን ኮከብ ሀሪ ኬን ለማዘዋወር በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ፉክክር ውስጥ እንደሚገቡ ይጠበቃል።ከወደ ጣሊያን የሚወጡ ዜናዎች ደግሞ ጁቬንትስም የእንግሊዛዊው አጥቂ ፈላጊ እንደሆነ እየዘገቡ ይገኛሉ።
(Tuttosport - inEnglish )






ቦሩሲያ ዶርትሙንድ እንግሊዛዊው አጥቂ ጄደን ሳንቾ ክለቡን መልቀቅ ከፈለገ ክረምት ላይ ሊለቀው ፈቃደኛ ነው።የ19 አመቱ አጥቂ በቼልሲ ፣ ሊቨርፑል እና ማንቸስተር ዩናይትድ ይፈለጋል።
(Standard)





አርሰናል እና ቶተንሃም ኦስትሪያዊውን አማካይ ማርሴል ሳቢዘር ከሌብዚኽ የማዘዋወር ፍላጎት አላቸው።ሳቢዘር በዚህ ሳምንት ቶተንሃም ላይ በሻምፒዮንስ ሊግ ሁለት ግብ ማስቆጠሩ ይታወሳል።
(Calcio Mercato - in English )





ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ በአርሰናል ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል።ጋቦናዊ ኢንተርናሽናል ስሙ በስፋት ከካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ጋር በመያያዝ ላይ ይገኛል።
(Mirror )





ባየርን ሙኒክ የቼልሲውን የመስመር አጥቂ ዊልያን ማዘዋወር ይፈልጋል።ብራዚላዊው የ31 አመት ተጨዋች በአመቱ መጨረሻ በስታንፎርድ ብሪጅ ያለው ኮንትራት ያበቃል።
( Sun )





የፈረንሳዩ እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝደንት የፓሪሰን ዤርመኑ ኪልያን ምባፔ ሀገሩን በ2020ው የቶክዮ ኦሊምፒክ እንዲወክል ፍላጎት አላቸው። 
(L'Equipe - in English )







No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...