አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ኒውካስትሎች በዚህ አመት ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን የወሳኙን ተከላካያቸውን ውል አራዝመዋል። ኒውካስትሎች የፊድሪኮ ፈርናንዴዝን ኮንትራት ለተጨማሪ አንድ አመት ነው ያራዘሙት።
የቱርኩ ቤሺክታሽ ግብፃዊውን ሞሀመድ ኤልኔኒን ተጨማሪ አንድ አመት ማቆየት እንደሚፈልጉ ተሰምቷል። ኤልኔኒ አሁን በውሰት እዛው ቱርክ ሲገኝ ክለቡ ቤሺክታሽ ዝውውሩን ቋሚ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸውም ይታወቃል።
የቀድሞው የዩናይትድ ኮከብ ፓርክ ጄሱንግ እና የአሁኑ የቶተንሀም ኮከብ ሰን ሁንግሚን እጃቸውን ለበጎ አድራጎት ዘርግተዋል።ሁለቱ ኮከቦች ደቡብ ኮሪያ ለሚገኙ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለተጠቁ ሰዎች 65.000ዩሮ ለግሰዋል።
ክሊያን ምባፔ ለዛሬ ምሽቱ ወሳኝ ጨዋታ ይደርሳል።በጉሮሮ ህመም ያለፉት ሁለት ቀናት ልምምድ ያመለጠው ምባፔ በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥሮ ምርመራዎችን አድርጓል። እናም ትናንት ለሊት ውጤቱ ይፋ ሲሆን ተጨዋቹ ለዛሬ ምሽቱ የዶርትመንድ ፍልሚያ ዝግጁ ነው።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የበላይ አስተዳዳሪዎች የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በዝግ ስታድየም ጨዋታዎች የማካሄድ ሀሳብ እንደሌላቸው ይፋ አድርገዋል።
ፖል ፖግባ በዩናይትድ አዲስ ፕሮጀክት ደስተኛ መሆኑ ተሰምቷል።እንደ M.E.N ዘገባ ከሆነ ፖግባ ተጨማሪ ኮንትራት በዩናይትድ ለመፈረም ፍላጎት አለው። በአዲሱ ኮንትራትም አሁን ከሚከፈለው 290.000ፓ. ወደ 400.000ፓእንዲያሳድጉለት ይፈልጋል።
በቀጣይ አመት በአውሮፓ መድረኮች ላይ ለመሳተፍ ትልቅ እድል ይዘው እየተፋለሙ የሚገኙት የኑኖ ስፕሪንቶ ወልቭሶች ኮሎምቢያዊውን ኮከብ ሀሜስ ሮድሪጌዝን እስከ £70m በማውጣት በክረምቱ ማስፈረም ይፈልጋሉ።
አስቶን ቪላዎች ከቸልሲ በውሰት የወሰዱትን የቀድሞውን እንግሊዛዊ የሌስተር ሲቲ ኮከብ ዳኒ ድሪንክ ወተርን ወደ ቸልሲ ሊመልሱት ዝግጁ ናቸው።
No comments:
Post a Comment