Sunday, March 22, 2020

የዕለተ እሁድ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

              አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ


የሊሉ የ21 አመት ኮከብ አማካይ ቦባክሪ ሶማሬ በተለያዩ የአውሮፓ ክለቦች እየተፈለገ ይገኛል።ፈረንሳዊውን ኮከብ ለማስፈረም የእንግሊዙ ማን.ዩናይትድ እና ሊቨርፑል የስፔኖቹ ሀያላኖች ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና የልጁ ፈላጊዎች ናቸው።





ኢንተር ሚላን ላውታሮ ማርቲኔዝን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ማጣታቸው የማይቀር ይመስላል። ይህንንም ተከትሎ የተለያዩ አጥቂዎችን ለማስፈረም እቅድ ይዘው እየተንቀሳቀሱ ይገኛል። ሙሉ በሙሉ የአጥቂ ፍላጎታቸውን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ አድርገዋል ማርቲኔዝን ለመተካት የአርሰናሉን ኦባሚያንግ የማን.ሲቲውን ጄሱስ እንዲሁም የዩናይትዱን ማርሻልን ማርቲኔዝን እንዲተኩላቸው ዝርዝር ውስጥ አስገብቷቸዋል።



ውስብስብ የሆነው የፊሊፔ ኩቲንሆ ዝውውር አሁን ሌላ ምእራፍ ከፍቷል።ባርሴሎናዎች ላውታሮ ማርቲኔዝን ከኢንተር ለማስፈረም ኩቲትሆን ለመስጠት ይፈልጋሉ ተብሏል። ኩቲንሆ በቸልሲ በጥብቅ ይፈለጋል ዩናይትድም የሳንቼዝ ተተኪ ማድረግ ይፈልጋል።





ቸልሲዎች አሁንም በክረምቱ የዝውውር መስኮት ቀዳሚ የአጥቂ ምርጫቸው ሙሳ ዴምቤሌ ነው። አሁን ላይ ስማቸው ከተለያዩ ተጨዋቾች ጋር ቢነሳም ግን እነሱ ግን ምርጫቸው ዴምቤሌ ነው ምናልባትም የሱ ዝውውር ማይሳካ ከሆነ የአርቢ ሌብዢኩን ቲሞ ዋርነር ነው።





ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ የናፖሊውን አማካይ ፋብያን ሩይዝን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።በ2018 ከሪያል ቤትስ መፈረሙ ይታወሳል። እንደ ካልቺዮ መርካቶ ዘገባ ከሆነ ሁለቱ ክለቦች ከተጨዋቹ ጋር ግንኙነት ጀምረዋል።




ማን.ሲቲ እና ሌስተር ሲቲ ቱርካዊውን የ17 አመቱን አሊ አክማንን ለማስፈረም ይፈልጋሉ። እንደ ፎቶ ስፖርት ዘገባ ከሆነ ዘንድሮ ቡራስፖር ዋናው ቡድን ተቀላቅሎ ጥሩ ጊዜን እያሳለ ይገኛል።





ማንችስተሮች በክረምቱ ሶስት የተለያዩ ቦታዎች ተጨዋቾችን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምረዋል። በተከላካይ ኩሊባሊ እና ጎዲንን እንዲሁም በአማካይ በርካታ ተጨዋቾችን እጩ ሲያረጉ በአጥቂ ስፍራ ኦባምያንግ ፣ ኬንን እና ዴምቤሌን ምርጫቸው አድርገዋል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...