Monday, March 23, 2020

የዕለተ ሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

           አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


የባርሴሎና ተጨዋቾች ክለቡ ከኮሮና ቫይረስ ምክንያት ገቢው በመቀነሱ ደሞዛቸው ለጊዜው እንዲቀንስተስማምተዋል።ካታላን ዘመሙ ስፖርት እንደዘገበው የክለቡ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ማሪያ ባርቶሚዮ ከሊዮኔል ሜሲ ፣ ሰርጂዮ ቡስኬትስ ፣ ጆርዲ አልባ እና ሰርጂ ሮቤርቶ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይተው ከስምምነት ደርሰዋል።
(Sport)





ምንም እንኳን በጁቬንትስ የተጠበቀውን ያህል ባይሆንም ፥ ማቲያስ ደ ላይት እና ባለቤቱ በጣሊያን እና ቱሪን ደስተኛ መሆናቸውን የባለቤቱ አባት ተናግረዋል።አባትየው ኔዘርላንዳዊው ተከላካይ 'ከአምስት እስከ፡አስር አመት' ሊቆይ ይችላልም ብለዋል።
(Goal)







ሪያል ማድሪድ በመጪው የዝውውር መስኮት የዎልቭሱን አጥቂ ራውል ሂሜኔስ ማዘዋወር ትልቅ ትልሙ ነው።ሎስብላንኮዎቹ ባሳለፍነው የዝውውር መስኮት ሉካ ዮቪችን በከፍተኛ ገንዘብ ያዘዋወሩ ቢሆንም በ24 ጨዋታዎች ሁለት ግብ ብቻ ነው ያስቆጠረው።በዚህም ምክንያት ነው ለዎልቭስ በ88 ጨዋታዎች 39 ግቦች ወደ አስቆጠረው ራውል ሂሜኔስ  ማድሪድ አይኑን ያዞረው።
(AS)







ፓሪሰን ዤርመን ፣ ሪያል ማድሪድ እና ማንቸስተር ሲቲ ስሎቫኪያዊውን የኢንተር ሚላን ተከላካይ ሚላን ስክሪኒያር ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።የ25 አመቱ ተከላካይ በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ሳንሲሮን መሰናበቱ አይቀሬ ይመስላል።
(Calciomercato - in Italian)






ባርሴሎና ፈረንሳዊውን አጥቂ አንቶኒ ግሬዝማን በቀጣዩ የዝውውር መስኮት በ€100ሚ. ለመሸጥ ተሰናድቷል።የካታላኑ ክለብ ከአንድ አመት በፊት ነበር ከአትሌቲኮ ማድሪድ በ€120ሚ. ያዘዋወረው።
(Sport)





አርሰናል እና ሊቨርፑል ፈረንሳዊውን የኢንትራክት ፍራንክፈርት ተከላካይ ኤቫን ኒዲካ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።
(Sky Sports)





አርጀንቲናዊው አጥቂ ጎንዛሎ ሂጎይን በጣሊያን ኳረንቲን ውስጥ እያለ አቋርጦ ወደ ሀገሩ ተመልሷል።ይህንን ያደረገው ደግሞ የካንሰር ህመምተኛ የሆነችውን እናቱን ለማስታመም ነው።
(Sun)





አርሰናል ተጨዋቾቹን በዚህ ሳምንት ወደ ልምምድ ሜዳ ይመለሱ ወይስ አይመለሱ በሚለው ጉዳይ ላይ እንደሚመክር ተነግሯል።በኮሮና ቫይረሳ ምክንያት ተጨዋቾች በቤታቸው እንደሚገኙ ይታወቃል።
(Mail)








ውድ ተከታታዮቻችን የዓለም ስጋት ስለሆነው የኮሮና ቫይረስ አንዳንድ መረጃዎችን እንስጣችሁ: 



መተላለፊያ መንገድ
• ከሰው ወደሰው በትንፋሽ አማካኝነት
• ከእንስሳት ወደ ሰው
ምልክቶች
• ሳል
• ትንፋሽ ማጠር
• ከፍተኛ የሆነ ሙቀት
• ብርድ ብርድ ማለት
• የሰውነት ድካም
• ራስ ምታት
• የመገጣጠሚያ እና የጡንቻ ህመም
ህክምና
• የሚያድን መድሃኒት የለውም ነገር ግን ከሱ ጋር ተያይዘው የሚመጡ
ምልክቶችን ማከም
• ፈሳሽ በደንብ መውሰድ
• የህመም ማስታገሻ መውሰድ
መከላከያ መንገድ
• የእጅ ንፅህናን መጠበቅ
• በሚያስሉ ወይም በሚያስነጥሱ ሰአት አፍን እና አፍንጫን በመሃረብ መሸፈን
• አፍንጫን አፍን እና አይንን ባልታጠበ እጅ አለመንካት
• ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች የሚያሰዩ ሰዎች ጋር ያለን ንክኪ ማስወገድ
• ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች ሲኖሩ በቶሎ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ


ምንጭ - ዶክተር አለ የፌስቡክ ገጽ







No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...