Monday, March 23, 2020

የዕለተ ሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

       አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ


ባሳለፍነው ሳምንት ስማቸው በኤሲ ሚላን 18 ወራት ከቀረው ግብ ጠባቂ ዶናሮማ ጋር ስማቸው ሲያያዝ የነበረው ኤቨርተኖች አሁን ላይ ተጨዋቹ ላይ ፍላጎት እንደሌላቸው እና ፒክፎርድ የቡድኑ የረጅም ጊዜ እቅድ እንደሆነ ታውቋል።





በተለያየ ጊዜ ስሙ ከብዙ ክለቦች ጋር የሚነሳው ሴኔጋላዊው ካሊዱ ኩሊባሊ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ናፖሊን መልቀቅ እንደሚፈልግ ተሰማ።ተጨዋቹ በዩናይትድ አሁን ላይ በጥብቅ ይፈለጋል ፥ በክረምቱም መልቀቁ እውን እየሆነ ነው።




ሊቨርፑሎች በክረምቱ ሎቭረንን በመልቀቅ በምትኩ የአ.ማድሪዱን ተከላካይ ሂሚኔዝን ማስፈረም ይፈልጋሉ።በአትሌቲኮ ማድሪድ እስከ 2023 ቀሪ ኮንትራት የሚቀረው ተጨዋቹ ሊቨርፑሎችን እስከ £12m የሚያስወጣቸው ይሆናል። ሊቨርፑሎች ከሂሚኔዝ በተጨማሪ የአርቢሌብዢኩን ዳዮት ኡፓምካኖ እና የኢንተር ሚላኑ አሌሳንድሮ ባስቶኒ ፈላጊ ናቸው ።




ባርሴሎና £100m ለሚያመጣ ክለብ አንቶኒዮ ግሪዝማንን ለመልቀቅ ዝግጁ ነው።ከአ.ማድሪድ ባርሳን ከተቀላቀለ ቡሀላ ጥሩ ጊዜን እያሳለፈ የማይገኘው ይህ ፈረንሳዊ አጥቂን በመልቀቅ በምትኩ ብር በመጨመር ኔይማርን ለመመለስ እጅጉን ፍላጎት አላቸው።አሁን ላይ ተጨዋቹ በዩናይትድ እና ፒኤስጂ እየተፈለገ ይገኛል።





ናፖሊ እና ባርሴሎና በቸልሲ በጥብቅ የሚፈለገውን የሳሱሎውን የ23 አመት  ቦጋ ሌላኛዎቹ ፈላጊዎች ሆነው ብቅ ብለዋል። ይህ ኮከብ  በዘንድሮ የውድድር አመት ለሳሱሎ 8ጎል እና 4 ለጎል የሚሆን ኳስ ማቀበል ችሏል።





ጁቬንቱስ በቡድኑ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉት እና በዚህ አመት ኮንትራታቸው ለሚጠናቀቀው ሶስት ተጨዋቾቹ አዲስ ኮንትራት ለመስጠት ፍላጎት አላቸው። ተጨዋቹም ብለስ ማቲዩዲ፣ጂያንሉጂ ቡፎን እንዲሁም  ጂኦርጂዮ ኬሌኒ ናቸው።




አርሰናል እና ሊቨርፑል በአንድ ተከላካይ ላይ ተፋጠዋል።በኢንትራንት ፍራንክፈረት ጥሩ አመት እያሳለፈ የሚገኘውን የ20 አመቱን ንዲካን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።ተጨዋቹ ከአርሰናል እና ሊቨርፑል በተጨማሪ በሲቪያ በቫሌንሲያ እንዲሁም በሁለቱ የሚላን ክለቦች ይፈለጋል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...