አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ባርሴሎና ዋነኛ ትልሙ አርጀንቲናዊውን አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ ማዘዋወር ሲሆን ይህ ካልሆነ ግን እንደ ሁለተኛ እቅድ ኦባማያንግን አስቧል።ጋቦናዊው አጥቂ በኤምሬትስ ለ18 ወራት የሚያቆይ ኮንትራት የቀረው ሲሆን ባርሴሎና ከፈለገውም ወደ ካታላን ለመጓዝ አይኑን አያሽም።
(Star)
ቼልሲ አዲሱ የፌሊፔ ኩቲንሆ ፈላጊ ሆኖ ብቅ ብሏል።ከባርሴሎና ለባየርን ሙኒክ በውሰት ተሰጥቶ በጀርመን የሚገኘው ብራዚላዊ ከቼልሲ በተጨማሪ በአርሰናል ፣ ቶተንሃም እና ማንቸስተር ዩናይትድም ይፈለጋል።
(Mirror)
ቦካ ጁኒየርስ የፓሪሰን ዤርመኑን አጥቂ ኤዲንሰን ካቫኒ በአመቱ መጨረሻ በነጻ ማዘዋወር ይሻል።ኡራጋዊያዊው አጥቂ በአመቱ መጨረሻ በፔዤ ያለው ኮንትራት ስለሚያበቃ ከኮንትራት ነጻ ይሆናል።
(El Pais)
ማንቸስተር ዩናይትድ በጥር ወር የዝውውር መስኮት በውሰት ከሻንጋይ ሺኖዋ ያዘዋወረውን የኦዲዮን ኤግሃሎን ውል ቋሚ ለማድረግ ጥረት እያደረገ ነው።ቀያይ ሰይጣኖቹ ለቻይናው ክለብ £15ሚ. ለመክፈል አቅደዋል።
(Mail)
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በአውሮፓ ሁሉ የእግር ኳስ ውድድሮች መቋረጣቸው ይታወሳል።ይህንንም ተከትሎ የቶተንሃሙ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ በስፐርስ ትሬኒንግ አቅራቢያ ለሚገኙ በእድሜ ለገፉ ሰዎች በራሳቸው ወጪ የምግብ እርዳታ እያደረጉ ነው።
(Football.London)
ኦስትሪያዊው የባየርን ሙኒክ ግራ መስመር ተከላካይ ዴቪድ አላባ በአመቱ መጨረሻ ወደ ማንቸስተር ሲቲ መጓዝን አይፈልግም።ከዚያ ይልቅ ሪያል ማድሪድን አሊያም ባርሴሎናን ለመቀላቀል ነው የሚሻው።
(Bild, via Sports Mole)
ማንቸስተር ሲቲ ጣሊያናዊውን የብሬሺያ አማካይ ሳንድሮ ቶናሊ በመጪው የክረምት የዝውውር መስኮት ለማዘዋወር አቅዷል።
(Corriere dello Sport, via Sport Witness)
No comments:
Post a Comment