Tuesday, March 24, 2020

የዕለተ ማክሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

                     አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ


ቸልሲዎች በክረምት ኬፓሪዛብላጋን በመሸጥ በምትኩ ሌላ ግብ ጠባቂ ለማሥፈረም ይፈልጋሉ። አሁን ላይ ቸልሲዎች ስማቸው ከ27 አመቱ ከበርንሌው ኒክ ፖፕ ጋር ተያይዟል።




ማንችስተር ሲቲዎች በሪያል ማድሪዱ ሀሜስ ሮድሪጌዝ ላይ ፍላጎት አሳይተዋል። በዚህ ሲዝን ብዙ የመሰለፍን እድል እያገኘ የማይገኘው ጀምስ ክረምት ላይ መልቀቁ አይቀሬ ሆኗል። እንደ መረጃው ከሆነ የሀሜስ ዝውውር በበርናንዶ ሲልቫ ቅይይርም ሊሆን ይችላል።




ባየርን ሙኒክ የፈረንሳዊውን የመስመር አጥቂ ኪንግስሊ ኮማን ኮንትራት ማደስ እንደሚፈልጉ ይፋ ሆኗል። ተጨዋቹ በሙኒክ እስከ 2023 ኮንትራት ያለው ሲሆን ሙኒኮች ተጨዋቹን ለረጅም ጊዜ በክለባቸው ለማቆየት ሲሉ ተጨማሪ ኮንትራት ሊሰጡት ዝግጁ ናቸው።




ሪያል ማድሪድ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የአጥቂ ክፍሉን ለማጠናከር የመጀመሪያ ምርጫቸው ኤርሊንግ ሀላንድ መሆኑ ተሰምቷል። ማድሪዶች ከሀላንድ በተጨማሪ የላውታሮ ማርቲኔዝ እና የቲሞ ዋርነርም ፈላጊ ናቸው።





ናፖሊዎች የላዚዮዉን የ30 አመቱን አጥቂ ቺሮ ኢሞቢሌን ማስፈረም እንደሚፈልግ ካልቺዮ መርካቶ አስነብቧል። በዚህ ሢዝን ድንቅ የውድድር አመትን እያሳለፈ የሚገኘው ኢሞቢሌ ከናፖሊ በተጨማሪ በበርካታ ክለቦችም እየተፈለገ ይገኛል።




ቦካ ጁኒየርስ በክረምቱ ኤዲሰን ካቫኒን ማስፈረም ይፈልጋሉ።በዚህ አመት ከፒኤስጂ ጋር ኮንትራቱ የሚጠናቀቀው ካቫኒ በክረምቱ በነፃ ወደ ፈለገበት ክለብ ማምራት ይችላል።ይህን ተከትሎ ቦካዎች ተጨዋቹን ለማምጣት ከማንኛውም ክለብ በላይ ፍላጎት ልጁ ላይ አሳይተዋል።




የፍራንክ ላምፓርዱ ቸልሲ ወጣቱን አማካይ ዴክላን ራይስን ከዌስትሀም ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው። እንደ መረጃው ከሆነ የዴክላን ራይስ እና የቸልሲው ማሰን ማወንት ቅርብ ጉዋደኝነት ዝውውሩን ለቸልሲዎች ቀለል እንደሚያረግላቸው ተነግሯል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...