አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ኦሊቨር ዡሩድ በክረምት ከቸልሲ መልቀቅ እንደሚፈልግ ለተጨዋቹ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ተናግረዋል በዚህ ሢዝን በቸልሲ ብዙም የመሰለፍ እድል ያላገኘው ዡሩድ ወደ ጣሊያን በማምራት በጥብቅ ለሚፈልጉት ኢንተር ሚላን አልያም ላዚዮን መቀላቀል ይፈልጋል።
እንደ ዴይሊ ሜይል ዘገባ ከሆነ የእንግሊዞቹ አርሰናል፣ ማን.ሲቲ እና ሊቨርፑል የ18 አመቱን የሻልክ ተከላካይ ማሊክ ቲሀውን ለማስፈረም ተፋጠዋል።ተጨዋቹ ክለቦቹን እስከ £7m እንደሚያስወጣቸው ታውቋል።
ማን.ዩናይትድ እና አርሰናል በባርሴሎናው ፈረንሳዊው ተከላካይ ሳሙኤል ኡምቲቲ ዝውውር ላይ ተፋጠዋል። ባርሴሎናዎች ለ26 አመቱ ፈረንሳዊ ተከላካይ እስከ £46m ይፈልጋሉ። ኡምቲቲ በዚህ ሲዝን ለባርሳ በላሊጋው 11 ጨዋታዎችን ብቻ ነው ያደረገው።
ማንችስተር ዩናይትዶች ካሊዱ ኩሊባሊን ከናፖሊ በክረምት ሚያስፈርሙ ከሆነ ክሪስ ስሞሊንግን ለሮማ አሳልፈው እንደሚሰጡ እርግጥ ሆኗል። ስሞሊንግ ከሮማ በተጨማሪ በአርሰናል በጥብቅ ይፈለጋል ዩናይትዶች ከተጨዋቹ £25m ይፈልጋሉ።
ቸልሲዎች በክረምቱ የዝውውር መስኮት የግራ መስመር ተከላካይ ለማስፈረም ዝግጁ ናቸው። የመጀመሪያ ምርጫቸው ቤን ቺልዌል ነው ነገር ግን አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ቸልሲዎች ፊታቸውን ወደ ስፔናዊው የጌታፌ የግራ መስመር ተከላካይ ማርክ ኩኩሬላ አዙረዋል።
ቶተንሀሞች ከሪያል ማድሪድ ጋር ተጨዋች ለመቀያየር ፍላጎት አላቸው። ጆዜ በማንችስተር እያለ ሲፈልገው የነበረውን ብራዚላዊውን ኤደር ሚላታኦን በቶተንሀም ማልያ ማየት ይፈልጋሉ። ይህን ተከትሎ ቶተንሀሞች ዳቪደን ሳንቼዝን ለማድሪድ በመስጠት በምትኩ ሚሊታኦን መውሰድ ይፈልጋሉ።
ጁቬንቱሶች በክረምቱ አጥቂ በማስፈረም ሂግዌንን መተካት ይፈልጋሉ።ስማቸው አሁን ላይ ከተለያዩ ኮከቦች ጋር እየተነሳ ይገኛል።ጁቬዎች የመጀመሪያ ምርጫቸው ብራዚላዊው የውሀ ሰማያዊዎቹ ኮከብ ጋብርኤል ጂሰስ ነው።ጂሰስ በዚህ ሲዝን ለማን.ሲቲ በ24 ጨዋታ 10ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።
No comments:
Post a Comment