አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ማንችስተር ሲቲዎች ሪያል ማድሪድን እና ባርሴሎናን በመርታት የናፖሊውን አማካይ ፋብያን ሩይዝን ለማስፈረም ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ ናቸው። እንደ ኮሬሮ ዴሎስፖርት ዘገባ ከሆነ ፔፕ በክረምቱ የመጀመሪያ ፈራሚው እንዲሆን ይፈልጋል። ናፖሊዎች ከሩይዝ እስከ £91m ይፈልጋሉ።

ባርሴሎናዎች ላውታሮ ማርቲኔዝን ለማስፈረም የተሻለ እድል እንዳላቸው የጣሊያኑ ቱቶ ስፖርት አስነብቧል። እንደ ዘገባው ከሆነ ሜሲ ላውታሮ ካምፕኑ እንዲደርስ እጅጉን ይፈልጋል። ባርሴሎናዎችም ለኢንተር ሚላን £65m + ቪዳል እና ሤሜዶን በመስጠት ላውታሮን ለመውሰድ ዝግጁ ናቸው።
የአርቢ ሌብዢኩ ተከላካይ ዳዮት ኡፓምካኖ በክረምት ክለቡን በመልቀቅ ወደ ሌላ ክለብ ለማምራት ሌብዢኮች ላይ ጫና እያሳደረ ይገኛል። ተጨዋቹ በብዙ የአውሮፓ ክለቦች ይፈለጋል።የእንግሊዞቹ ቶተንሀም እና አርሰናል እንዲሁም ባርሴሎና እና ባየርን ሙኒክ የተጫዋቹ ፈላጊ ሲሆኑ ሌብዢኮች ከ21 አመቱ ተከላካይ £55m ይፈልጋሉ።
የጣሊያኑ ብሬሺያዎች አዲሱ ፔርሎ እየተባለ ሚጠራውን አማካያቸውን ሳንድሮ ቶናሊ የመሸጫ ዋጋ ይፋ አድርገዋል። ብሬሺያዎች ከተጨዋቹ £46m ይፈልጋሉ። ተጨዋቹ እዛው በጣሊያን ክለቦች እጅጉን ይፈለጋል።
በጥር ዩናይትድን በውሰት የተቀላቀለው እና ጥሩ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘውን ኦዲዮን ኢግሀሎን ተጨማሪ አመታት በቻይና እንዲቆይ አዲስ ኮንትራት አቅርበውለታል። ክለቡ ሻንጋይ ሽንዋ ለተጨዋቹ ተጨማሪ ሁለት አመት ኮንትራት እና 400,000ፓ. አቅርበውለታል።
ቶተንሀሞች ከኢንተር ሚላን በክረምት መልቀቁ እውን የሆነውን የ33አመቱን ኡራጋዊው ተከላካይ ዲያጎ ጎዲንን ለማሥፈረም ዝግጁ ሆነዋል።ተጨዋቹ በዩናይትድ ቢፈለግም ቶተንሀሞች ዩናይትዶችን በመቅደም ጎዲንን ለማስፈረም ዝግጁ ናቸው።
ባየርን ሙኒኮች ጀርመናዊውን ኮከብ ሊዩሪስ ሳኔን ለማስፈረም ለማንችስተር ሲቲዎች አዲስ የዝውውር ሀሳብ ይዘው መተዋል።እንደ ቢልድ ዘገባ ከሆነ ሙኒኮች የመስመር ተከላካዩን ዳቪድ አላባን ሰቶ ሳኔን ለመውሰድ ይፈልጋሉ።
No comments:
Post a Comment