Friday, March 27, 2020

የዕለተ ቅዳሜ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች

             አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ


የጋርዲዮላው ሲቲ በክረምት የተከላካይ ክፍሉን ለማጠናከር ፊቱን ወደ ጣሊያናዊው የጁቬንቱስን ተከላካይ ሊዮናርዶ ቦኑቺ አዙረዋል።እንደ ካልቺዮ መርካቶ ዘገባ ከሆነ ሲቲዎች ተጨዋቹን በቀላሉ እንደሚያገኙት ተማምነዋል።





ማንችስተር ዩናይትድ ፣ ቦካ ጁኒየርስ ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ እንዲሁም ኢንተር ሚላን በፒኤስጂው አጥቂ ላይ ተፋጠዋል።በክረምቱ ከኮንትራት ነፃ የሚሆነው እና በፒኤስጂ መቆየት የማይፈልገውን ካቫኒን ለማስፈረም ክለቦቹ ካሁኑ ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።





ቸልሲዎች ቤን ቺልዌልን ለማስፈረም ሲሉ ተጨዋቾችን ለመልቀቅ ዝግጁ ሆነዋል።ቸልሲዎች በኢንተር ሚላን በውሰት የሚገኘውን ሞሰስን አና ኤመርሰንን ለኢንተር ሚላን ለመሸጥ ፍቃደኛ ሆነዋል።በተጨማሪም ፔድሮንም በክረምት ለመልቀቅ ዝግጁ ናቸው።





የአንቶኒዮ ኮንቴው ኢንተር ሚላን በዚህ አመት ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን የቶተንሀም ሆትስፐሩን ቤልጄማዊውን ተከላካይ ቬርቶጋንን በነፃ ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው።እንደ ካልቺዮ መርካቶ ዘገባ ከሆነ ኮንቴ ጎዲንን ለመልቀቅ ዝግጁ ስለሆኑ ተጨዋቹን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።




ታማኙ ጋዜጠኛ ጂአሉካ ዲማርዚዮ ትናንት ማምሻውን እንዳስነበበው ከሆነ ቸልሲ በተለያዩ ክለቦች የሚፈለገውን የኢሳፓኞሉን ወጣት ኒኮላስ መላሜድን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።ቸልሲዎች ተጨዋቹን ከሌሎች ክለቦች በላይ ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል።





ፊሊፔ ኩቲንሆ በክረምት ወደ ሴሪያ የመመለስ እድል እንዳለው ካልቺዮ መርካቶ አስነብቧል።በባርሳ ካልተሳካ ጊዜ በኋላ ወደ ሙኒክ አምርቶ አመርቂ ሚባል እንቅስቃሴ እያደረገ የማይገኘው ኩቲንሆ በክረምት ወደ ጁቬንቱስ አልያም ወደ ቀድሞ ክለቡ ኢንተር ሚላን ሊመለስ እንደሚችል ተነግሯል።




አርሰናሎች ሳይታሰብ ሀሜስ ሮድሪጌዝን ከበርናቦ ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል። ከሙኒክ ከውሰት ከተመለሰ በኋላ በማድሪድ የመሰለፍ እድልን እያገኘ የማይገኘው ሀሜስ በክረምት መልቀቁ አይቀሬ ሆኗል። አርሰናልም ከተለያዩ ክለቦች ጋር ተፎካክሮ ተጫዋቹን ለማስፈረም ጥረት እንደሚያደርግ ዴይሊ ሜይል አስነብቧል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...