Sunday, March 22, 2020

የዕለተ እሁድ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                  አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


የጁቬንትሱ ፓውሎ ዲባላ በኮሮና ቫይረስ መያዙን ይፋ አድርጓል።በተጨማሪም የቀድሞው የኤሲ ሚላን ሌጀንድ ፓውሎ ማልዲኒ እና ልጁ በቫይረሱ ተይዘዋል።ጣሊያን በቫይረሱ በከፍተኛ እና አስከፊ መልኩ እየተጠቃች ትገኛለች።
(Goal)





ዝላታን ኢብራሒሞቪች ሲዝኑ ሲያልቅ ኤሲ ሚላንን እንደሚለቅ እየተነገረ ነው።የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ቺፍ ኦፊሰሩ ዝቮንሚር ቦባን በመባረራቸው ደስተኛ ባለመሆኑ ነው።ስዊድናዊው ግዙፍ አጥቂ በጥር ወሩ የዝውውር መስኮት ነበር ከሜጀር ሊግ ሶከሩ ኤል.ኤ ጋላክሲ ወደ ኤሲ ሚላን የተዘዋወረው።
(Sport Mediaset)




ኢድ ውድ ዋርድ በፖል ፖግባ ጉዳይ ከወኪሉ ሚኖ ራዮላ ጋር ድርድር ሊጀምሩ ነው።ራዮላ ከማንቸስተር ዩናይትድ አመራሮች ጋር ያለው ነገር መልካም ባይሆንም ለመደራደር ግን ፍቃደኛ ነው።የ27 አመቱ ፈረንሳዊ አማካይ በሪያል ማድሪድ እና ጁቬንትስ ይፈለጋል።
(Mirror)





የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ብራዚላዊውን አማካይ ፌሊፔ ኩቲንሆ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።በውሰት ባየርን ሙኒክ የሚገኘው ኩቲንሆ የባቫሪያው ክለብ ውሉን ቋሚ ሊያደርግለት ስላልቻለ ወደ ባርሴሎና ለመመለስ የሚገደድ ሲሆን ባርሴሎና ሊሸጠው ይሻል።የእንግሊዞቹ ቼልሲ ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ ፣ አርሰናል እና ቶተንሃም ደግሞ ፈላጊዎቹ ናቸው።
(Mirror)




ክሎፕ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ማዘዋወር ከሚፈልጋቸው ተጨዋቾች ዋነኛው የናፖሊው አማካይ ፋቢያን ሩይዝ ይገኝበታል።የ23 አመቱ አማካይ በስታዲዮ ሳን ፓውሎ እንዲሰነብት የቀረበለትን ውልም ውድቅ አድርጓል።ሊቨርፑል ለተጨዋቹ £74ሚ. ያሰናዳ ሲሆን ሪያል ማድሪድ ፣ ባርሴሎና ፣ ባየርን ሙኒክ እና ማንቸስተር ዩናይትድም ይፈልጉታል።
(Express)





ብራዚላዊው ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር እና ሆላንዳዊው ተከላካይ ቨርጅል ቫን ዳይክ በሊቨርፑል ለተጨማሪ አመታት የሚያቆያቸውን ኮንትራት ሊፈርሙ ነው።
(Goal)






የብራዚላዊው ኮከብ ኔይማር ወኪሎች ለባርሴሎና አመራሮች ተጨዋቹ ፈረንሳይን መልቀቅ እንደሚሻ እና ወደ ካምፕ ኑ መመለስ እንደሚፈልግ ነግረዋቸዋል።
(Star)





ማንቸስተር ዩናይትድ ጋቦናዊውን የአርሰናል አጥቂ ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ ለማዘዋወር £50ሚ. አሰናድቷል።ኢንተር ሚላን እና ባርሴሎናም የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸው።
(Metro)






በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የእግር ኳስ ውድድሮች መቋረጣቸውን ተከትሎ ፓሪሰን ዤርመን አጥቂውን ኪሊያን ምባፔን አዲስ ውል እንዲፈርም ለማግባባት ጊዜ አግኝቷል።ፈረንሳዊው ተጨዋች እስከ 2022 በፓርክ ደ ፕሪንስ የሚያቆይ ኮንትራት አለው።
(Marca)







ውድ ተከታታዮቻችን የዓለም ስጋት ስለሆነው የኮሮና ቫይረስ አንዳንድ መረጃዎችን እንስጣችሁ: 



መተላለፊያ መንገድ
• ከሰው ወደሰው በትንፋሽ አማካኝነት
• ከእንስሳት ወደ ሰው
ምልክቶች
• ሳል
• ትንፋሽ ማጠር
• ከፍተኛ የሆነ ሙቀት
• ብርድ ብርድ ማለት
• የሰውነት ድካም
• ራስ ምታት
• የመገጣጠሚያ እና የጡንቻ ህመም
ህክምና
• የሚያድን መድሃኒት የለውም ነገር ግን ከሱ ጋር ተያይዘው የሚመጡ
ምልክቶችን ማከም
• ፈሳሽ በደንብ መውሰድ
• የህመም ማስታገሻ መውሰድ
መከላከያ መንገድ
• የእጅ ንፅህናን መጠበቅ
• በሚያስሉ ወይም በሚያስነጥሱ ሰአት አፍን እና አፍንጫን በመሃረብ መሸፈን
• አፍንጫን አፍን እና አይንን ባልታጠበ እጅ አለመንካት
• ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች የሚያሰዩ ሰዎች ጋር ያለን ንክኪ ማስወገድ
• ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች ሲኖሩ በቶሎ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ


ምንጭ - ዶክተር አለ የፌስቡክ ገጽ

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...