አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ባርሴሎናዎች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ኔይማርን ለመመለስ እጅጉን ፍላጎት አላቸው። ባሳለፍነው ክረምት ኔማርን ለማዘዋወር ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም ውድቅ እንደተደረገባቸው ይታወሳል።አሁን ላይ ግን ልጁን እንደሚያመጡ ተማምነዋል።ኔይማርም ቢሆን ወደ ቀድሞ ቤቱ መመለስ እንደሚፈልግ ተሰምቷል።
ለረጅም አመታት በባይርን ሙኒክ የተሳካ ጊዜ ያሳለፈው የመስመር ተከላካዩ አላባ በክረምቱ ወደ ስፔን እንደሚያቀና ተሰምቷል። ባርሴሎና ልጁን ለማስፈረም ፍላጎቱ ከፍ ያለ ነው ሪያል ማድሪድም ልጁን ለማስፈረም ይፈልጋል።
ጁቬንቱስ እና ናፖሊ በአንድ ተጨዋች ላይ ተፋጠዋ። በ2017 ወደ ባየርን ሙኒክ ያመራውን ፈረንሳዊውን ቶሊሶን ለማስፈረም ይፈልጋሉ። ሁለቱ የጣሊያን ክለቦች ለተጨዋቹ £35m ለመክፈል ዝግጁ ናቸው።
ባርሴሎና፣ ፒኤስጂ፣ ማ.ዩናይትድ በኦባምያንግ ላይ ተፋጠዋል።ከዚህ በፊት ተጨዋቹ ወደ ባርሴሎና ያመራል ቢባልም አሁን ላይ ግን ፒኤስጂ እና ዩናይትድ ፉክክሩን ተቀላቅለዋል።
ሊቨርፑል እና ባርሴሎና የሬንሱን የ17 አመት አማካይ ካማቪንጋን ለማዘዋወር ፍላጎት አላቸው። ከዚህ በፊት ተጨዋቹ በአርሰናል እና በዩናይትድ እንደሚፈለግ ይታወሳል። ይህ ወጣት ኮከብ ክለቦቹን እስከ £50m እንደሚያስወጣቸው ታውቋል።
አርሰናል እና ቶተንሀም ኮንትራቱ በ2021 የሚጠናቀቀውን የሊቨርፑሉን ተከላካይ ዲያን ሎቭረንን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።በክረምቱ ሊቨርፑልን ከሚለቁ ተጨዋቾች ውስጥ አንዱ የሆነው ሎቭራን በጣሊያን ክለቦችም ይፈለጋል።
ቸልሲዎች ከጣሊያን ሴሪያ ተጨዋቾችን ለማስፈረም £200m እንደመደቡ ተነግሯል።የተጨዋቾቹ ምርጫ ሲሰማ ከጁቬ የመልቀቅ እድል የሌለው ፒያኒች በተጨማሪም ቸልሲዎች ብለስ ማቲዩዲ ቤንታኩር ራምሴን እስከ £55m ላውታሮ ማርቲኔዝን ከኢንተር ሚላን £101m እንዲሁም ግብ ጠባቂውን ዶናሮማን ከኤሲ ሚላን £47m ለማውጣት ዝግጁ ናቸው።
No comments:
Post a Comment