Saturday, March 21, 2020

የዕለተ ቅዳሜ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                 አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)

ባርሴሎና በዘንድሮው አመት ትልቅ ትኩረት ከሰጠባቸው ጉዳዮች መሀከል የሊዮኔል ሜሲን ውል ማራዘም ዋነኛው ነው።ሜሲ በአሁኑ ሰዓት እስከ ሰኔ 2021 የሚያቆይ ኮንትራት ያለው ሲሆን ባርሴሎና ልክ እንደ አንድሬስ ኢኒየስታ ያቀረበለትን 'የህይወት ዘመን ኮንትራት' ለመፈረም ግን ዳተኛ ሆኗል።
(AS)





ሰርጂዮ ራሞስ ሪያል ማድሪድ ከ30 አመት በላይ በሆኑ ተጨዋቾች ላይ ያለውን ፖሊሲ እንዲቀይር ተጽዕኖ እየፈጠረ ይገኛል።እንደሚታወቀው የፍሎረንቲኖ ፔሬዝ አስተዳደር ከ30 አመት በላይ ለሆኑ ተጨዋቾች የሚሰጠው ኮንትራት አንድ አመት ብቻ ሲሆን የ34 አመቱ ራሞስም ይህንን ነው እየተቃወመ ያለው።
(Marca)




የቀድሞው የቼልሲ ሌጀንድ ጆን ቴይሪ ሰማያዊዎቹ ጄደን ሳንቾን እንዲያዘዋውሩ መክሯል።ቼልሲ በአሁኑ ሰዓት አውሮፓ ውስጥ ካሉ ድንቅ ታዳጊዎች አንዱ የሆነውን እንግሊዛዊ ለማዘዋወር በተደጋጋሚ እየሞከረ መሆኑ ይታወቃል።ሳንቾ 2017 ላይ ቦሩሲያ ዶርትሙንድን ከተቀላቀለ አንስቶ በ90 ጨዋታዎች 31 ግብ አስቆጥሮ 36 ኳስ ደግሞ ለግብ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
(Goal)






ባርሴሎና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እንደ ማንኛውም ክለብ ሁሉ ገቢው በእጅጉ ስለቀነሰ የተጨዋቾቹ ደሞዝ ላይ በጊዜያዊነት የደሞዝ ቅነሳ ሊያደርግ ነው።የፈረንሳዩ ማርሴ በዚህ ወር ደሞዝ ለተጨዋቾች እንደማይከፍል ያሳወቀው በዚህ ሳምንት ነበር።
(Mundo Deportivo)





ኔይማር በመጪው የክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ባርሴሎና እንደሚመለስ በስፋት እየተነገረ ይገኛል።ኔይማር 2019 ላይ ወደ ባርሴሎና ለመመለስ ብዙ ጥሮ የነበረ ቢሆንም ፓሪሰን ዤርመን ግን እንዲሳካ አልፈቀደም ነበር።
(Sport)






ሊቨርፑል ባቡከሬ ሴሙሬን ለማዘዋወር አሁንም ከሊል ጋር በመደራደር ላይ ነው።ሆኖም ወጣቱን አማካይ ለማዘዋወር ከባርሴሎና ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል።
(Sport)





ማንቸስተር ዩናይትድ የኒማኒያ ማቲችን ውል ለማራዘም ከተጨዋቹ ጋር ድርድር ላይ ነው።ቀያይ ሰይጣኖቹ ለሰርቢያዊው አማካይ የሁለት አመት ኮንትራትን ከሳምንታዊ £140,000 ጋር ነው ያቀረቡለት።
(Sun)





ጁቬንትስ ጣሊያናዊውን አማካይ ጆርጊንሆ ከቼልሲ ለማዘዋወር ከገንዘብ በተጨማሪ ቦሲኒያዊውን አማካይ ሚራለን ፒያኒች መስጠት ይፈልጋል።
(Corriere dello Sport, via Sun)





በውሰት ማንቸስተር ዩናይትድን የተቀላቀለው ናይጄሪያዊው አጥቂ ኦዲዮን ኤግሃሎ በሳምንት ከሚያገኘው £180,000 በተጨማሪ ጎል ሲያስቆጥር £8,000 ቡድኑ ሲያሸንፍ ደግሞ £9,000 እየተከፈለው ነው።ይህም የሆነው ኮንትራቱ ላይ እንዲህ ያለ ውል ስለሰፈረ ነው።
(Sun)







ውድ ተከታታዮቻችን የዓለም ስጋት ስለሆነው የኮሮና ቫይረስ አንዳንድ መረጃዎችን እንስጣችሁ: 



መተላለፊያ መንገድ
• ከሰው ወደሰው በትንፋሽ አማካኝነት
• ከእንስሳት ወደ ሰው
ምልክቶች
• ሳል
• ትንፋሽ ማጠር
• ከፍተኛ የሆነ ሙቀት
• ብርድ ብርድ ማለት
• የሰውነት ድካም
• ራስ ምታት
• የመገጣጠሚያ እና የጡንቻ ህመም
ህክምና
• የሚያድን መድሃኒት የለውም ነገር ግን ከሱ ጋር ተያይዘው የሚመጡ
ምልክቶችን ማከም
• ፈሳሽ በደንብ መውሰድ
• የህመም ማስታገሻ መውሰድ
መከላከያ መንገድ
• የእጅ ንፅህናን መጠበቅ
• በሚያስሉ ወይም በሚያስነጥሱ ሰአት አፍን እና አፍንጫን በመሃረብ መሸፈን
• አፍንጫን አፍን እና አይንን ባልታጠበ እጅ አለመንካት
• ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች የሚያሰዩ ሰዎች ጋር ያለን ንክኪ ማስወገድ
• ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች ሲኖሩ በቶሎ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ


ምንጭ - ዶክተር አለ የፌስቡክ ገጽ

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...