(Mundo Deportivo)
ማን ዩናይትድ ለፖል ፖግባ £100ሚ. የሚያቀርብ ክለብ ካገኘ ለመሸጥ አያመነታም።ሪያል ማድሪድ እና ጁቬንትስ የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸው።
(Sun)
ሪያል ማድሪዶች ያለባቸውን የአጥቂ ችግር ለመግታት ፊታቸውን ወደ አርጀንቲናዊው ግብ አዳኝ ማውሮ ኢካርዲ አዙረዋል። በፓርክ ዴፍሬንስ በውሰት ጥሩ አመት እያሳለፈ የሚገኘውን ኢካርዲ በክረምቱ ለማዘዋወር እስከ £64m ሊያወጡ ይገባቸዋል። ተጨዋቹን ፒኤስጂዎችም ማስቀረት ይፈልጋሉ።
ቶተንሀሞች የሊቨርፑሉን ተከላካይ ዲያን ሎቭረንን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።የቫንዳይክ የጎሜዝ እና የማቲፕን ጥምረት የማግኘት እድል የተነሳው ሎቭራን በክረምቱ መልቀቁ እውን ሆኗል።ሎቭራን ከቶተንሀም በተጨማሪ በላዚዮ በኤሲሚላን በአርሰናል በሊዮን ይፈለጋል።
ናፖሊ እና ኢንተርሚላን በአይቮሪኮስታዊው ተጨዋች ተፋጠዋል። እንደ ካልቺዮ መርካቶ ዘገባ ሁለቱ ክለቦች የሳሱሎውን አማካይ ጀርሚ ቦጋን ለማስፈረም ነው የተፋጠጡት እንደምናስታውሰው ተጨዋቹ በ2018 ነበር ከቸልሲ ሳሱሎን የተቀላቀለው።
ባርሴሎናዎች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ትልልቅ ዝውውሮችን እንደሚያደርጉ ከአሁኑ እየተነገረ ይገኛል። እንደ Sport ዘገባ ከሆነ ባርሳዎች የመሀል ተከላካይ የመስመር ተከላካይ(ፉል ባክ) የመሀል ተጨዋች እንዲሁም የመስመር አጥቂ ነው ለማስፈረም የሚፈልጉት።
የአንቾሎቲው ኤቨርተን ፔሌግሪኒን ከሮማ ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው። እንደ ካልቺዮ መርካቶ ዘገባ ከሆነ አንቾሎቲ የተጨዋቹ አድናቂ እንደነበሩ እና በጣሊያን ሳሉ ለናፖሊ እንዲፈርም ይፈልጉ ነበር አሁን ላይ ኤቨርተኖች ልጁን ለማስፈረም ዝግጁ ናቸው።
ሪ.ማድሪድ፣ ባርሴሎና እና ማን.ዩናይትድ በወጣቱ ኦማር ቤይዝ ላይ እንደተፋጠጡ ኤክስፕረስ ዘግቧል። ቱርካዊው የ16 አመት ተጨዋች በፊነርባቼ እስከ 2021 የሚያቆየው ውል አለው ነገር ግን ተጨዋቹ ከሶስቱ ለአንዳቸው መፈረሙ አይቀሬ ነው።
ቶተንሀሞች አይናቸውን ወደ ኪዊፒአሩ ኮከብ ኢቤርቺ ኢዚ ጥለዋል። ይህ የ21 አመት ኮከብ ቶተንሀሞችን እስከ £20m ያስወጣቸዋል ተብሏል። ተጨዋቹ ከቶተንሀም ውጭ በክርስቲያል ፓላስ እና በሼፍልድ ይፈለጋል። ኢዚ ባሳለፍነው ክረምት በፖቸቲንሆም እንደሚፈለግ የሚታወስ ነገር ነው።
ውድ ተከታታዮቻችን የዓለም ስጋት ስለሆነው የኮሮና ቫይረስ አንዳንድ መረጃዎችን እንስጣችሁ:
መተላለፊያ መንገድ
• ከሰው ወደሰው በትንፋሽ አማካኝነት
• ከእንስሳት ወደ ሰው
ምልክቶች
• ሳል
• ትንፋሽ ማጠር
• ከፍተኛ የሆነ ሙቀት
• ብርድ ብርድ ማለት
• የሰውነት ድካም
• ራስ ምታት
• የመገጣጠሚያ እና የጡንቻ ህመም
ህክምና
• የሚያድን መድሃኒት የለውም ነገር ግን ከሱ ጋር ተያይዘው የሚመጡ
ምልክቶችን ማከም
• ፈሳሽ በደንብ መውሰድ
• የህመም ማስታገሻ መውሰድ
መከላከያ መንገድ
• የእጅ ንፅህናን መጠበቅ
• በሚያስሉ ወይም በሚያስነጥሱ ሰአት አፍን እና አፍንጫን በመሃረብ መሸፈን
• አፍንጫን አፍን እና አይንን ባልታጠበ እጅ አለመንካት
• ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች የሚያሰዩ ሰዎች ጋር ያለን ንክኪ ማስወገድ
• ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች ሲኖሩ በቶሎ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ
ምንጭ - ዶክተር አለ የፌስቡክ ገጽ
No comments:
Post a Comment