Tuesday, March 17, 2020

የዕለተ ማክሰኞ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

          አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ


ኤሲ ሚላኖች በፒኤስጂ እና በጁቬንቱስ በጥብቅ የሚፈለገውን እና ሳንሴሮን በክረምት መልቀቅ የሚፈልገውን ግብ ጠባቂውን ዶኖሮማን ለመተካት የቶሪኖውን ሲሪጉን እና የናፖሊውን አሌክስ መርትን ምርጫቸው እንዳረጉ ካልቺዮ መርካቶ አስነብቧል።





ባርሴሎናዎች አርትሮ ቪዳልን የላውታሮ ማርቲኔዝ የዝውውር አንድ አካል አድርገው ወደ ኢንተር መላክ እንደሚፈልጉ ተሰምቷል ።ባርሴሎናዎች አሁን ላይ ከፒኤስጂ እና ከሲቲ በማርቲኔዝ ጉዳይ ትልልቅ ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።




ቸልሲዎች አሁን የሙሳ ዴምቤሌ ፈላጊ ናቸው። የክረምቱ የዝውውር መስኮት ሲከፈት ከሌሎች ክለቦች በመቅደም ተጨዋቹን ለማስፈረም ዝግጁ ናቸው። በተጨማሪም ቸልሲዎች የአርቢ ሌብዢኩን ቲሞ ዋርነርን ይፈልጋሉ።




ፖል ፖግባ በክረምት ዩናይትድን የመልቀቁ እድል ጠባብ ነው።ትናንት ወደ ልምምድ የተመለሰው ፖግባ ከብሩኖ ጋር ለመጣመር እጅጉን እንደጓጓ ተሰምቷል።በተጨማሪም በዩናይትድ ያለውን ውል ለማደስ ንግግር ሊጀምር መሆኑ ተሰምቷል።




ሌተን ቤንስ በኤቨርተንን ኮንትራቱ ሲጠናቀቅ ወደ አሜሪካው ሜጀር ሊግ ሶከር ማምራት እንደሚፈልግ ተናገረ። ለረጅም አመታት በኤቨርተን ያገለገለው ይህ ድንቅ የግራ  መስመር ተከላካይ በኤቨርተን የ12ወራት ኮንትራት ይቀረዋል። እሱን ሲጨርስ ወደ ኤልኤ ጋላክሲ ማምራቱ እውን እየሆነ ነው።




ባየርን ሙኒክ ለጊዜያዊው አሰልጣኝ ሀንስ ፍሊክ ተጨማሪ ኮንትራት ለመስጠት ድርድር ላይ ናቸው። በተጨማሪም ሙኒኮች በቡድኑ ረዘም ላለ ጊዜ ለተጫወቱት ቶማስ ሙለር ፣  ኑዌር  እንዲሁም አላባ አዲስ ኮንትራት አቅርበውላቸዋል።




በአርሰናል አዲስ ኮንትራት ለመፈረም 330,000 የጠየቀው እና ውድቅ የተደረገበት ኦባምያንግ በክረምቱ ወደ ባርሴሎና ማምራት እንደሚፈልግ ተነግሯል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...