Monday, March 16, 2020

የዕለተ ሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

      አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


እንግሊዛዊው የ26 አመት የቶተንሃም አጥቂ ሀሪ ኬን ምንም እንኳን ሁለቱ የማንቸስተር ከተማ ክለቦች ማን ዩናይትድ እና ማን ሲቲ በጥብቅ ቢፈልጉትም እርሱ ግን ወደ ጣሊያኑ ክለብ ጁቬንትስ መጓዝ ነው የሚሻው።
(Tuttosport via Express)





ጁቬንትስ ፖርቱጋላዊውን ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለተጨማሪ አመታት በቱሪን ለማቆየት አዲስ የውል ማራዘሚያ ኮንትራት ሊያቀርብለት ነው።አሮጊቷ ለአምስት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ ኮከብ እስከ 2024 የሚያቆይ ኮንትራት ነው ለማቅረው የወጠነችው።
(Tuttosport via Mail)






ማንቸስተር ሲቲዎች የፕሪሚየር ሊጉን በኮሮና ቫይረስ የጨዋታ መራዘሞች ተከትሎ ሙሉ ትኩረታቸውን ኬቬን ደ ብሮይነ እና ራሂም ስተርሊንግን በኮንትራት ጉዳይ ማወያየት ሆኗል።
(Sun)




ማንቸስተር ዩናይትድ በውሰት ከቻይናው ሻንጋይ ሺኖዋ ያዘዋወረውን ናይጄሪያዊውን ኦዲዮን ኤግሃሎ በቋሚነት ኦልድ ትራፎርድ ለማቆየት እየሰራ ነው።ቀያይ ሰይጣኖቹ ይህንን ለማድረግ £6ሚ. ለቻይናው ክለብ መክፈል ይጠበቅባቸዋል።
(Mail)





ሪያል ማድሪድ ሆላንዳዊውን የአያክስ አማካይ ዳኒ ቫን ዴቢክ ለማዘዋወር ያደረገው ሙከራ አለመሳካቱን ተከትሎ ማን ዩናይትድ ይህንን ዕድል በመጠቀም ለማዘዋወር እየሰራ ነው።
(Marca - in Spanish)





ሚኬል አርቴታ £60ሚ. የሚገመተውን የዌስት ሀሙን አማካይ ኢሳ ዴዮፕ ወደ አርሰናል ማስመጣት ይፈልጋል።ፈረንሳዊው ተጨዋች በማንቸስተር ዩናይትድም ይፈለጋል።
(Metro)




ባርሴሎና በቀጣዩ የዝውውር መስኮት አራት ተጨዋቾችን ለማዘዋወር ዕቅድ አለው።እነዚህ ተጨዋቾች የመሀል ተከላካይ ፣ የመስመር ተከላካይ ፣ አማካይ እና ቀጥተኛ አጥቂ መሆኑን ካታላን ዘመሙ ሚዲያ sport አስነብቧል።
(SPORT)










No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...