Sunday, March 15, 2020

የዕለተ እሁድ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች




ጁቬንቱሶች የሮናልዶን ኮንትራት ለማራዘም ፍላጎት አላቸው።ከማድሪድ ጁቬዎችን ከተቀላቀለ ቡሀላ ይሄንን ሲዝን ጨምሮ ሁለት አመት ያሳለፈው እና ኮንትራቱ እስከ 2022 የሚቆየውን ሮናልዶን ተጨማሪ ሁለት አመት ለማስፈረም እንደሚፈልጉ እና ንግግር ለመጀመር ዝግጁ መሆናቸው ተሰምቷል። 




ቸልሲዎች የባርሴሎናውን የመስመር ተጨዋች ኩኩሬላን ለማስፈረም በሚደረገው ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።የ21 አመቱ ተጨዋች አሁን በጌታፌ በውሰት እያሳለፈ ይገኛል።ተጨዋቹን ለማስፈረም ከቸልሲ በተጨማሪ ናፖሊ ቦሩሲያ ሞንቼግላድባ እና ባየርን ሌቨርኩሰን ይፈለጋል።




ቶተንሀም እና ሌስተር ሲቲ የላዚዮ ግብ ጠባቂ ላይ አይናቸውን ጥለዋል። የ24 አመቱን ቶማስ ስትራኮሻን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ፉክክር ውስጥ ገብተዋል። ግብ ጠባቂው በላዚዮ እስከ 2022 ኮንትራት አለው።



ቦሩሲያ ዶርትመንዶች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ቤልጄማዊውን የፒኤስጂ የቀኝ መስመር ተከላካይ ቶማስ ሙንየርን የማግኘት እድላቸው ሰፊ ነው ፥ ተጨዋቹ በዚህ አመት መጨረሻ ኮንትራቱ ይጠናቀቃል።




ሪያል ማድሪዶች ሳዲዮ ማኔን በክረምቱ የዝውውር ለማስፈረም ይፈልጋሉ። ሊቨርፑሎች ተጨዋቹን በቀላሉ ይለቁታል ተብሎ ባይጠበቅም ማድሪዶች ግን ልጁን ለማግኘት የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተነግሯል ማድሪዶች ማኔን ለማስፈረም £140m አዘጋጅተዋል።




ኒውካስትሎች ፊታቸውን ወደ እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ ተከላካይ ፊል ጆንስ አዙረዋል። በተለያየ ጊዜ ዩናይትድን ይለቃል ሲባል የሰነበተው ጆንስ ይህ አመት የመጨረሻው ሳይሆን አልቀረም። ኒውካስትሎች ለጆንስ እስከ £12m ለማውጣት ዝግጁ ናቸው ጆንስን ዌስትሀምም ይፈልገዋል።




አርሰናሎች በውሠት ከማድሪድ ያስፈረሙትን ስፔናዊውን አማካይ ዳኒ ሴባዮስን ዝውውር ቋሚ ለማድረግ £35m ለማቅረብ ዝግጁ ናቸው።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...