Saturday, March 14, 2020

የዕለተ እሁድ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች

          አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር የአውሮፓ ዋንጫን እስከ ዲሴምበር ቀኑን ለማራዘም አቅዷል።ይህን የሚያደርገው ደግሞ ሁሉም ሊጎች እንዲጠናቀቁ ጊዜ ለመስጠት ነው ተብሏል።
(Sunday Telegraph)





ፓሪሰን ዤርመኖች ብራዚላዊው አጥቂ ኔይማር በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ ባርሴሎና እንደሚመለስ ይጠብቃሉ።የዝውውር ሒሳቡም €150ሚ. ገደማ ነው።
(Marca - in Spanish)





ማንቸስተር ዩናይትድ ለሼፍልድ በውሰት የሰጠውን ግብ ጠባቂ ዲን ሄንደርሰንን ወደ ክለቡ ለመመለስ አስቧል።የ23 አመቱ ግብ ጠባቂ በተለይ በቼልሲ በጥብቅ የሚፈለግ ሲሆን ዩናይትድ ግን ወደ ክለቡ መልሶ በሳምንት £100,000 ሊከፍለው ወስኗል።
(The Sun)





ሊቨርፑል በቀጣዩ ክረምት አራት ተጨዋቾችን እንደሚለቅ ይጠበቃል።እነዚህ ተጨዋቾች ዤርዳን ሼኪሪ ፣ዲያን ሎቭረን ፣ ናትናኤል ክላይን እና አዳም ላላና ናቸው።ተጨዋቾቹ ኮንትራታቸው ስለሚያበቃ በነጻ ነው ከሊቨርፑል የሚለቁት።
(Liverpool Echo)





ሪያል ማድሪድ በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ዋነኛ ዕቅዱ የሊቨርፑሉን ሳዲዮ ማኔ ማዘዋወር ነው።ሊቨርፑል ሴኔጋላዊውን ኮከብ የመሸጥ ፍላጎት ባይኖረውም ሎስብላንኮዎቹ ግን ከወዲሁ £140ሚ. አሰናድተዋል።
(Mirror)





ፖርቱጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ አንድ በጎ ምግባር ሰርቷል።ሮናልዶ በትውልድ ሀገሩ የሚገኙ ሆቴሎቹን በጊዜያዊነት ወደ ህክምና ተቋምነት ቀይሯቸዋል።ሁሉም ህመም የሚሰማው ሰው ወደ ጊዜያዊ ህክምና መስጫው ገብቶ በነጻ መታከም የሚችል ሲሆን ሙሉ ወጪውን የዶክተሮቹን እና ነርሶቹን ክፍያ ጨምሮ ሮናልዶ የሚሸፍን ይሆናል።
(Bleacher)




ሊዮኔል ሜሲ ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ መልዕክቱን አስተላልፏል።ሜሲ ለሁሉም የሰው ልጅ ጊዜ ከባድ መሆኑን ተናግሮ ፥ ሁሉም ሰው ቤተሰቡን እና ራሱን እንዲጠብቅ አደራ ብሏል።
(Goal)









በጥር ወሩ የዝውውር መስኮት ማን ዩናይትድን የተቀላቀለው ፈርናንዴዝ በክለቡ ውስጥ ትልቅ አዎንታዊ ለውጥ ማምጣቱን ብዙዎች የሚስማሙበት ሲሆን በቀያይ ሰይጣኖቹ ደጋፊዎች ዘንድም ዝነኛ ሆኗል።

ከስካይ ስፖርትስ ጋር ቆይታ ያደረገው ብሩኖም የዩናይትድ ደጋፊዎች ባደረጉለት አቀባበል መደሰቱን ተናግሮ በስሙ የሚዘምሩለት ነገርም ይበልጥ ደስ እንዳለው ተናግሯል።

በ£47ሚ. ከስፖርቲንግ ሊዝበን ማን ዩናይትድን ከተቀላቀለ አንስቶም በዘጠኝ ጨዋታዎች ላይ መሰለፍ የቻለ ሲሆን ሶስት ግቦችን አስቆጥሮ አራት ኳስ ደግሞ ለግብ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።


ከስካይ ስፖርትስ ጋር በነበረው ቆይታም የሚከተለውን ብሏል
"ከሌላ ሀገር መጥቶ ትልቅ ክለብን ከትልቅ ተጨዋቾች ጋር መቀላቀል ትልቅ ለውጥ አለቅ።ዩናይትድን የመቀላቀል ዕድሉን ሳገኝ ሁለቴ እንኳን ለማሰብ አልሞከርኩም።"


ክርስቲያኖ ሮናልዶ ማን ዩናይትድን ለመቀላቀሉ ትልቅ ምሳሌ እንደሆነውም ተናግሯል።
"ሮናልዶ ለኔ ትልቅ ምሳሌዬ ነው።ሮናልዶ በመመልከት ትጀምርና ከዛ፡የሚጫወትበትን ክለብ ታያለህ።ያ ክለብ ሁሉንም ማሸነፍ እንደሚችል ታያለህ በስተመጨረሻ በዛ ክለብ መጫወት ህልምህ ይሆናል።"



ስለ ደጋፊዎቹ
"ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ደጋፊዎቹ የሰጡኝ ድጋፍ አስደናቂ ነበር።ገና በመጀመሪያ ወ'ሬ ያሳዩኝ ድጋፍ ትልቅ መነሳሻ ሆኖኛል።"

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...