Saturday, March 14, 2020

የዕለተ ቅዳሜ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

         አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ


ጣሊያናዊው የኔፕልሶች አምበል የሆነው ሊዮሬንዞ ኢንሴኚ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አስቸጋሪ ጊዜ ላይ ለምትገኘው የትውልድ ከተማው 100,000ዩሮ ለተለያዩ ሆስፒታሎች ሰቷል።





ቶተንሀሞች በተለያየ ጊዜ በዩናይትድ ራዳር ውስጥ የገባውን ማርሴል ሳቢልዘርን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ሳቢልዘር ከቶተንሃም በተጨማሪ በአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች ይፈለጋል።




አርሰናሎች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ትልልቅ ዝውውሮችን እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። አሁን ላይ በወጣው መረጃ አርቴታ የወልቭሱን ኳስ አቀጣጣይ ፖርቱጋላዊ ኮከብ ዲያጎ ጆታን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል።



በጥሩ የዝውውር መስኮት በ6 ወር የውሰት ውል ኦልትራፎርድ የደረሰው ኦዲዮን ኢጋሎህ ውሉ ሲጠናቀቅ ተጨማሪ ኮንትራት ሊሰጠው እንደሚችል ለክለቡ ቅርብ የሆነው M.E.N አስነብቧል።




በዚህ ሲዝን ከቸልሲ ጋር ኮንትራቱ የሚጠናቀቀው ዊሊያን ከለንደን መውጣት እንደማይፈልግ ተሰምቷል። የመጀመሪያ ምርጫው ቸልሲን ከለቀቀ አርሰናልን አርጓል። ነገር ግን አርሰናልን ለመቀላቀል መስፈርት አስቀምጧል እሱም አርሰናል የቀጣይ አመት የቻምፒየንስ ሊግ ቦታን ማግኘት ነው።




የሼፊልዱ አሰልጣኝ ክሪስ ዋይልደር በውሰት በክለባቸው የሚገኘውን እንግሊዛዊ ኮከብ በረኛን ዲያን ሄንደርሰንን በክረምቱ በሼፊልድ ተጨማሪ ኮንትራት ለማስፈረም ለማንችስተር ይፋዊ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።




ፍራንክ ላምፓርድ በዩናይትድ በዚህ አመት ኮንትራቱ ሚጠናቀቀውን ፖርቱጋላዊ ኮከብ አንድሬ ጎሜዝን ለማስፈረም እየተከታተለው ይገኛል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...