አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
አርሰናል እና ቶተንሀሞች በሮማ በውሰት እየተጫወተ የሚገኘውን የማንችስተር ዩናይትዱን ተከላካይ ክሪስ ስሞሊንግ ለማስፈረም ከምንግዜውም በላይ ተፋጠዋል። ዩናይትዶች ተጨዋቹ ላይ £25m መለጠፋቸውን ተከትሎ አሁን ሚገኝበት ሮማ ዝውውሩን ቋሚ እንደማያደርጉት ታውቋል።ይህንንም ተከትሎ የሰሜን ለንደን ክለብ የሆኑት ቶተንሀም እና አርሰናል £25m ከፍለው ማስፈረም ይፈልጋሉ።
ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ከፖቸቲንሆ ሰዎች ጋር ለመምከር ቀጠሮ ይዘዋል። ለማድሪድ ቅርብ የሆነው AS እንዳስነበበው ከሆነ ማድሪዶች በዚዳን የወደፊት ቆይታ ላይ አሁንም እርግጠኛ አይደሉም። ፔሬዝም ስራ ፈቶ የሚገኘውን ፖቸቲንሆን ይህ የውድድር አመት ሲጠናቀቅ ወደ ቤርናባው ለማምጣት ስራዎችን ከአሁኑ ጀምረዋል።
በጀርመን ቡንደስሊጋ ድንቅ የውድድር አመት እያሳለፈ የሚገኘው የአርቢ ላይብዢኩ ጀርመናዊ ኮከብ ቲሞ ዋርነር በክረምቱ ጀርመንን በመልቀቅ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንደሚዘዋወር ፍንጭ ሰቷል። ለየትኛው ክለብ እንደሚፈርም ይፋ አላደረገም ወደ ሊቨርፑል የመግባት እድሉ ሰፊ ነው ተጨዋቹ በዩናይትድ፣ በሲቲ እና በቸልሲ ይፈለጋል።
ከሰሞኑ ከቸልሲጋር የነበረውን የአዲስ ኮንትራት ድርድር ያቋረጠው ዊሊያን ቀጣይ አመት ማረፊያው የት እንደሆነ እንደማያቅ ተናግሯል። ቸልሲ ለዊሊያን 2አመት ኮንትራት ቢያቀርብለትም ዊሊያን ግን ከ3 አመት በታች ኮንትራት መፈረም እንደማይፈልግ ተናግሮ ድርድሩ መቋረጡ ይታወሳል።
ዩናይትዶች በክረምቱ ለሁለት ተጨዋቾች £100m ለማውጣት መዘጋጀታቸውን M.E.N ዛሬ ጠዋት አስነብቧል። ዩናይትዶች ለአስቶንቪላዊ አማካይ ጃክ ግሪሊሽ £70m እና ለበርኒንግሀሙ የ16 አመት ጁዴ ቤሊንግሀ £30m ለመክፈል ዝግጁ ናቸው።
በዚህ አመት ኮንትራቱ ሲጠናቀቅ ማንችስተር ሲቲን እንደሚለቀቅ የተረጋገጠው ስፔናዊው አማካይ ዴቪድ ሲልቫ በክረምቱ ማረፊያው የዴቪድ ቤካሙ ኢንተር ሚያሚ ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል።
አርሰናል በክረምቱ የዝውውር መስኮት የፒኤስጂውን የግራ መስመር ተከላካይ ላይቪን ኩርዝዋን በነፃ ለማስፈረም ከአሁኑ ድርድው ሊጀምሩ ነው።
የስዋሬዝ እድሜ መግፋት እና የዴምቤሌ ተደጋጋሚ ጉዳት ያሳሰባቸው ባርሴሎናዎች በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ብዙ ገንዘቦችን በማውጣት የቀድሞ ኮከባቸውን ኔይማርን እንዲሁም አዲሱን አርጀንቲናዊ ኮከብ ላውታሮ ማርቲኔዝን በክረምት ለማስፈረም ቀዳሚ ኢላማቸው አድርገዋቸዋል።
No comments:
Post a Comment