Wednesday, March 11, 2020

የዕለተ ረቡዕ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

               አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ትናንት ምሽት በሻምፒዮንስ ሊግ ሁለት ጨዋታዎች የተደረጉ ሲሆን ወደ ሩብ ፍጻሜ ያለፉ ክለቦችም ታውቀዋል።የጀርመኑ ራ.ቢ ሌብዚኽ ቶተንሃምን 3ለ0 በድምር 4ለ0 በመርታት ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።ጆዜ ሞሪንሆም በዚህ ውጤት እየተተቹ ነው።በሌላው ጨዋታ አታላንታ ከሜዳ ውጪ ቫሌንሲያን 4ለ3 አሸንፎ በድምር 8ለ4 በሆነ ውጤት የጋስፔሪኒ ክለብ ወደ ሩብ ፍጻሜው አልፏል።
(BBC)




የስፔኑ ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድ የ28 አመቱን ፈረንሳዊ ኢንተርናሽናል አሌክሳንደር ላካዜት ከአርሰናል የማዘዋወር ፍላጎት እንዳለው ሙንዶ ዲፖርቲቮ አስነብቧል።
(Mundo Deportivo - in Spanish)





ባርሴሎና ጀርመናዊውን የአር.ቢ ሌብዚኽ አጥቂ ቲሞ ዋርነር ከአርጀንቲናዊው የኢንተር ሚላን አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ ቀጥሎ የማዘዋወር ፍላጎት አለው።
(Mundo Deportivo - in Spanish)





ትናንት ምሽት ፈረንሳዊው የፔዤ አጥቂ ኪልያን ምባፔ የኮሮና ቫይረስ ምልክት የሚመስል ነገር በማሳየቱ ወደ ህክምና መጓዙ ተጠቁሞ ፥ ብዙሀኑ የእግር ኳስ ቤተሰብ ድንጋጤ ውስጥ ገብቶ ነበር።ሆኖም ዛሬ በወጣ መረጃ ምባፔ ከበሽታው ነጻ ነው።
(L'Equipe - in French)




ምንም እንኳን ከዚህ በፊት ሞክሮ ባይሳካለትም ሊቨርፑል አሁንም ቤልጄሚያዊውን የአንደርሌክት የ17 አመት አጥቂ ጄሬሚ ዶኩ ለማዘዋወር ጥረት ማድረጉን ይቀጥላል።
(Het Nieuwsblad, via Star)





ሪያል ማድሪድ ዚነዲን ዚዳንን በአርጀንቲናዊውን ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆ አሊያም በጣሊያናዊ ማሲሚሊያኖ አሌግሪ ለመተካት እየሰራ ነው።ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ዚዳንን ለማሰናበት አቅደዋል።
(Marca - in Spanish)





የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር (UEFA) በኮሮኖ ቫይረስ ስጋት ምክንያት የ2020ውን የአውሮፓ ዋንጫ ጊዜ ለማዘዋወር እያሰበበት ነው።የየሀገራቱ ፌድሬሽኖችም እንዲራዘም ጥያቄ እያቀረቡ ነው።
(Tuttosport - in Italian)




ስሙ ከሌሎች ክለቦች ጋር በስፋት ሲያያዝ የሰነበተ ቢሆንም ፖል ፖግባ በአሁኑ ሰዓት ሀሳቡን ቀይሮ በማን ዩናይትድ የመቆየት ፍላጎት አድሮበታል።የዚህ ምክንያቱ ደግሞ የብሩኖ ፈርናንዴዝን መምጣት ተከትሎ ያለውን የቡድኑን መነቃቃት በመመልከቱ ነው።
(Daily Mail)





ጆዜ ሞሪንሆ ክለባቸው በክረምቱ የዝውውር መስኮት የተለየ ተጨዋች እንደማያስፈርም ተናግረዋል።የተጎዱ ተጨዋቾቻችን ስለሚመለሱ ተጠናክረን በቀጣዩ አመት እንቀርባለንም ብለዋል።
(BT Sport)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...