አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ለማስታወቂያ ስራ ሀገረ እንግሊዝ የሚገኘው ታዋቂው ቦክሰኛ ፍሎይድ ሜይ ዌዘር ኒውካስትል ዩናይትድን የመግዛት ፍላጎት እንዳለው ጠቁሟል።
ሜይ ዌዘር ሀምሳ ጊዜ ተቧቅሶ አንድም ጊዜ እንዳልተረታ ይታወቃል።
(Goal)
ማንቸስተር ዩናይትድ ብሩኖ ፈርናንዴዝን ማዘዋወሩ ቡድኑን በእጅጉ እንደጠቀመው የግራ መስመር ተከላካዩ ሉክ ሾው ተናግሯል።ፈርናንዴዝ በጥር ወሩ የዝውውር መስኮት ቀያይ ሰይጣኖቹን ከተቀላቀለ አንስቶ በአምስት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሁለት ግብ አስቆጥሮ ሶስት ኳስ ደግሞ ለግብ አመቻችቶ አቀብሏል።
(Goal)
በውሰት ቦሩሲያ ዶርትመንድ የሚገኘው አሽረፍ ሀኪሚ ሪያል ማድሪድ የሚፈልገው ከሆነ በአመቱ መጨረሻ ያለ ምንም ማቅማማት ወደ ሳንቲያጎ በርናቢዮ እንደሚመለስ ተናግሯል።ሞሮኳዊው ተከላካይ በዶርትመንድ ቤት ለሁለት አመታት በውሰት ለመቆየት የተስማማው 2018 ላይ ነበር።
(Goal)
የማንቸስተር ዩናይትዱ ምክትል ሊቀ መንበር ኢድ ውድ ዋርድ ሀሪ ኬንን በተመለከተ ከቶተንሃሙ መሪ ዳኒ ሌቪ ጋር ሊነጋገሩ ነው።በጥር ወሩ የዝውውር መስኮት ኖርዌጂያኑን ኤርሊንግ ሃላንድ ለማዘዋወር ያደረገው ጥረት ያልተሳካለት ዩናይትድ ክረምት ላይ እንግሊዛዊውን ሀሪ ኬን ለማዘዋወር ይሻል።ሆኖም ሞሪንሆ ኬን ክለቡን እንዲለቅ አይፈልጉም።
(Evening Standard)
ዴቪድ ሲልቫ በአመቱ መጨረሻ ውሉ ስለሚጠናቀቅ ከማንቸስተር ሲቲ እንደሚለቅ የሚጠበቅ ሲሆን ዴቪድ ቤካም በባለቤትነት በያዘው ኢንተር ሚያሚም በጥብቅ ይፈለጋል።
(Daily Star)
ብራዚላዊው ዊልያን ስለ ቀጣይ የእግር ኳስ ህይወቱ እርግጠኛ እንዳልሆነ ተናገረ።ዊልያን በአመቱ መጨረሻ በቼልሲ ያለው ውል የሚጠናቀቅ ሲሆን በአዲስ ኮንትራት ዙሪያም በመደራደር ላይ ነው።
(Evening Standard)
ማንቸስተር ሲቲዎች ምንም እንኳን በሻምፒዮንስ ሊግ ለሁለት ተከታታይ አመታት እንዳይሳተፉ ቢታገዱም ፥ አርጀንቲናዊው የምንጊዜም የክለቡ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ኩን አጉዌሮ በክለባቸው እንደሚቆይ ተስፋ አድርገዋል።
(Evening Standard)
ባርሴሎና ጀርመናዊው ግብ ጠባቂው ማርክ አንድሬ ቴር ስቴገን ለክለቡ ታምኖ አዲስ ኮንትራት እንዲፈርም ይፈልጋል።ጀርመናዊው ግብ ጠባቂ በቼልሲ በጥብቅ እየተፈለገ ነው።
(Sport)
No comments:
Post a Comment