አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ለአስር ሳምንታት በጉዳት ምክንያት ከሜዳ ርቆ የነበረው ፖል ፖግባ ወደ ልምምድ ሜዳ የተለመሰ ሲሆን በትጋት ተጨማሪ ልምምድን በግሉም እየሰራ ነው ሲል MEN አስነብቧል።
ኦሌ ጉናር ሶልሻየርም አሁን ፖግባን በተመለከተ ስላለው መረጃ ሲናገር "ፖግባ በሀኪሞቹ በመታገዝ በግሉ ልምምድ እየሰራ ነው ፥ ሆኖም እስከ ቀጣዩ ሳምንት ከዋናው ቡድን ጋር በጋራ ልምምድን አይሰራም።ወደ አቁሙ ለመመለስ ጊዜ ያስፈልገዋል ፥ ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅም እናያለን። " ብሏል።
ፖግባ ትናንት ምሽት ኦልድ ትራፎርድ ላይ የታደመ ሲሆን ከጨዋታው በኋላም 'ማንቸስተር ቀይ ናት" ሲል ኢንስታ ግራም ገጹ ላይ ለቅቆ ነበር።
No comments:
Post a Comment