አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
የማንቸስተር ዩናይትዱ አምበል ሀሪ ማጉዌር የብሩኖ ፈርናንዴዝ መምጣት ቡድናቸውን በእጅጉ እንዳሻሻለው ተናግሯል።ማጉዌር ፖርቱጋላዊውን አማካይ "ድንቅ ስብዕና ያለው ፥ እንዲሁም የቡድኑ አውራ ተጨዋች" ሲል ገልጾታል።
(Manchester Evening News)
ሪያል ማድሪድ ስፔናዊውን ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባልጛ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ለማዘዋወር ይሰራል።ቼልሲ በአንጻሩ የባርሴሎናዊ ጀርመናዊ ግብ ጠባቂ ማርክ አንድሬ ቴር ስቴገን ፈላጊ ነው።ይህ ካልተሳካ ደግሞ ባለቤትነቱ የማንቸስተር ዩናይትድ የሆነውን ዲን ሄንደርሰንን ለማዘዋወር ይጥራል።
(Star)
ፔፕ ጋርዲዮላ ለቤልጄሚያዊው ድንቅ አማካይ ኬቨን ደ ብሮይነ አዲስ የውል ማራዘሚያ ኮንትራት እንዲቀርብለት ይፈልጋል።አዲሱ ኮንትራት ለ28 አመቱ አማካይ በሳምንት £350,000 ያስገኝለታል።
(Express)
አርሰናል የቀድሞውን ተጨዋቹን ዶኔል ማሌንን ለማዘዋወር እየሰራ ነው።ሆላንዳዊው የ21 አመት አጥቂ 2017 ላይ ነበር ወደ ፒ.ኤስ.ቪ ኤንድሆቨን የተቀላቀለው።
(Le10Sport)
ኦሌ ጉናር ሶልሻየር ማን ዩናይትድ ለሻምፒዮንነት ለመወዳደር ሁለት ወይም ሶስት ተጨዋቾችን ማስፈረም እንደሚጠበቅባቸው ተናግሯል።ዩናይትድ በዚህ አመት ከአስር አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ደርስ መልስ ማን ሲቲ አሸንፏል።
(ESPN)
ፈረንሳዊው አጥቂ ኦሊቪየር ዢሩ ባለፈው የጥር ወር የዝውውር መስኮት ወደ ቶተንሃም ሊጓዝ የሚችልበት ዕድል የነበረ ቢሆንም ባለ መፈለጉ አለመሳካቱን ተናግሯል።
(90 Min)
ስሙ ከዝውውር ጋር በስፋት እየተያያዘ የሚገኘው ጋቦናዊው አጥቂ ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ በአርሰናል ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል።የ30 አመቱ አጥቂ በዚህ ሰዓት የአርሰናል ወሳኝ ተጨዋች መሆኑን በተደጋጋሚ አስመስክሯል።
(Mirror)
አርጀንቲናዊው የጁቬንትስ አጥቂ ፓውሎ ዲባላ ወኪሉ ከማንቸስተር ዩናይትዱ መሪ ኢድ ውድ ዋርድ ጋር በመነጋገር ላይ ሳለ ንግግሩን እንዲያቋርጥ አድርጓል።
(Calciomercato, via Mirror)
No comments:
Post a Comment