አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ቶተንሀሞች የሪያል ቤትሱ የመስመር ተጨዋች የሆነው ዲያጎ ሌንዝ ላይ ፍላጎት አሳይተዋል።እንደ ዶን ባሎን ዘገባ ከሆነ ጆዜ የ19 አመቱ ወጣት ኮከብ £13m ሊያሶጣቸው እንደሚችል ተሰምቷል።
ሮማዎች በክረምት የሚፈልጉት የአጥቂ ዝውውር ካልተሳካ ዲያጎ ኮስታን ከአትሌቲኮ ማድሪድ ለማስፈረም ይፈልጋሉ።ሮማዎች ኮስታት ከዚህ ቀደም በ2013 እና በ2018 ለማስፈረም ሞክረው ሳይሳካላቸው እንደቀረ መረጃው አያይዞ ጠቅሷል።
ሪያል ማድሪዶች ወጣቱ ኡራጋዊው የመሀል ሜዳ ኮከባቸው ፌዴሪኮ ቫልቬርዴ ላይ ማንም ማይደፍረውን የዝውውር ሂሳብ ለጥፈዋል። ማድሪዶች ተጨዋቹን ፈልገው ሚመጡ ክለቦች እስከ £450m መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ይፋ አድርገዋል። ከሰሞኑ ማንችስተር ዩናይትድ የተጨዋቹ ፈላጊ መሆኑ መሰማቱ ይታወቃል።
የጣሊያኑ ላዚዮ በክረምት ቸልሲን መልቀቁ እውን የሆነውን ስፔናዊውን ፔድሮ ሮድሪጌዝን ለማስፈረም ይፈልጋል።እንደ ጋዜጣ ዴሎ ስፖርት ዘገባ ከሆነ የተጨዋቹ ኮንትራት በክረምት ስለሚጠናቀቅ ላዚዮች ከሌላ ክለቦች ቀድመው ተጨዋቹን ለመውሰድ ትልቅ ስራ ይጠብቃቸዋል። ከፔድሮ በተጨማሪ ዡሩድንም ከቸልሲ ማስፈረም ይፈልጋሉ።
ሲቪያዎች ከስቶክ ሲቲ ወደ ሊቨርፑል ከተዘዋወረ በኋላ የመሰለፍ እድል ያጣውን ስዊዘርላንዳዊውን ዤርዳን ሻኪሪን በክረምት ለማስፈረም ይፈልጋሉ። ሊቨርፑሎችም ተጨዋቹን በክረምት ለመልቀቅ ዝግጁ ናቸው።
ቸልሲዎች በክረምቱ የሚሳካላቸው ከሆነ ሞሮካዊውን ፉል ባክ አሽራፍ ሀኪሚክን ከሪያል ማድሪድ ለማስፈረም ይፈልጋሉ።ተጨዋቹ በዚህ የውድድር አመት ለቦሩሲያ ዶርትመንድ በውሰት ተሰቶ ድንቅ ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል።
ሉካ ዮቪች በአርሰናል ራዳር ውስጥ ገብቷል። ሰርቢያዊው የ22 አመቱ አጥቂ በክረምቱ መልቀቁ አይቀሬ ሆኗል። ተጨዋቹ ከአርሰናል በተጨማሪ በቸልሲ እና በቶተንሀም ይፈለጋል።
ማድሪዶች ምን ነካቸው 450m ነው ከእውነት የራቀ መረጃ ነው
ReplyDelete