Thursday, March 5, 2020

የዕለተ ሐሙስ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

              አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)




ፓሪሰን ዤርመን ኪልያን ምባፔን በማቆየት ኔይማርን የመሸጥ ዕቅድ አለው።ፔዤ ሁለቱም ተጨዋቾች በፓርክ ደ ፕሪምስ እንዲቆዩ የሚሻ ቢሆንም ይህ የማይሳካ ከሆነ ግን ከኔይማር ይልቅ ምባፔን ይመርጣል።እስከ 2022 በፔዤ የሚያቆይ ኮንትራት ያለው ፈረንሳዊው ኮከብ ምባፔ በሪያል ማድሪድ በጥብቅ ይፈለጋል።
(As)





ማርክ አንድሬ ቴር ስቴገን በባርሴሎና ለተጨማሪ አመታት የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ሊፈራረም ነው።ቴር ስቴገን አዲስ ውሉን ሲያድስ የውል ማፍረሻው €180ሚ. እንደሚሆን ይጠበቃል።
(Deportivo reporter Alfredo Martinez)





ፖል ፖግባ በማንቸስተር ዩናይትድ ሊቆይ ይችላል።ምንም እንኳን የፈረንሳዩ አማካይ ስም በስፋት ከሪያል ማድሪድ እና ጁቬንትስ በኦልድ ትራፎርድ የሚቆይበት ዕድልም አለ።የብሩኖ ፈርናንዴዝ መምጣት ደግሞ ምክንያት ሊሆን ይችላል።
(Daily Star)




የኤርሊንግ ሀላንድ አባት ልጃቸው ስፔን ላሊጋ ላይ ቢጫወት ደስተኛ እንደሚሆኑ ተናገሩ። "የልጄ ስም ከመቶ በላይ ቡድኖች ጋር ሲያያዝ ቆይቷል።ነገር ግን ስፓኒሽ ላሊጋ ለልጄ ጥሩ ሊግ ይመስለኛል ፥ ታላላቅ ክለቦችም ይገኙበታል" ነው ያሉት።ይህንንም ተከትሎ የሀላንድ ስም በስፋት ከሪያል ማድሪድ ጋር እየተያያዘ ይገኛል።
(Goal)






የቀድሞው የእግር ኳስ ኮከብ ሮናልዲንሆ ጎቾ በፓራጓይ መታሰሩ ይፋ ሆኗል።ብራዚላዊው የቀድሞው ኮከብ በፓራጓይ ህገ-ወጥ የፓራጓይ  ፓስፖርት ይዞ ነው የተገኘው።ፓስፖርቱ ላይ ሮናልዲንሆ ዜግነቱ ፓራጓዊ እንደሆነ ይጠቅስ እንደነበርም ታውቋል።
(La Nacion)





የ26 አመቱ እንግሊዛዊ አጥቂ ሀሪ ኬን በቶተንሃም አዲስ ውል የመፈረም ፍላጎት የለውም።ኬን ማንቸስተር ዩናይትድ የሚፈልገው ከሆነ ቀያይ ሰይጣኖቹን የመቀላቀል ፍላጎትም አለው።
(Goal)





የአር.ቢ ሌብሲኹ  ፕሬዝደንት ክለባቸው ጀርመናዊውን አጥቂ ቲሞ ዋርነር በተመለከተ ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ ከየትኛውም ክለብ እንዳልቀረበለት ተናግረዋል።የ23 አመቱ አጥቂ በሊቨርፑል ፣ ቼልሲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ይፈለጋል።
(Mirror)





የጀርመኑ ክለብ ቦሩሲያ ዶርትመንድ እንግሊዛዊውን የመስመር አጥቂ ጄሰን ሳንቾ ለመሸጥ ያቀደው እስከ €140ሚ. ድረስ ነው።ሳንቾ በበርካታ ሐያላን ክለቦች እንደሚፈለግ ይታወቃል።
(Bild - in German)






ብራዚላዊው የመስመር አጥቂ ዊልያን በቼልሲ አዲስ ውል ለመፈረም ፍላጎት የለውም።በአመቱ መጨረሻ በስታንፎርድ ብሪጅ ያለው ኮንትራት የሚያበቃው ዊልያን ምናልባትም ወደ ቶተንሃም የሚጓዝበት ዕድል አለ።
(UOL)





ኢንተር ሚላን በክረምቱ የዝውውር መስኮት አርጀንቲናዊውን አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ ለባርሴሎና የሚሸጥ ከሆነ በምትኩ ከካታላኑ ክለብ ሶስት ተጨዋቾችን ይፈልጋል።
(Mundo Deportivo, via Mail)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...