አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ሪያል ማድሪድ የቀድሞውን የቶተንሃም አሰልጣኝ ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆ በማነጋገር ላይ ይገኛል።ሎስብላንኮዎቹ በስፐርስ ድንቅ ቡድን የሰራውን አርጀንቲናዊ የዚነዲን ዚዳን ምትክ የማድረግ ፍላጎት አላቸው።
(Independent)
ቶተንሃም በቀጣዩ አመት በሻምፒዮንስ ሊግ መሳተፍ የማይችል ከሆነ በርካታ ወሳኝ ተጨዋቾቹን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ሊያጣ እንደሚችል ይጠበቃል ፥ ዋነኛው ደግሞ እንግሊዛዊው አጥቂ ሀሪ ኬን ነው።
(Telegraph)
ባርሴሎና ፣ ሊቨርፑል እና ሪያል ማድሪድ የ20 አመቱን የቫሌንሲያ የመስመር አጥቂ ፌራን ቶረስ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።ወጣቱ ተጨዋች በዘንድሮው አመት ድንቅ ጊዜን በላሊጋው በማሳለፍ ላይ ነው።
( El Mundo Deportivo via Daily Mail )
የማንቸስተር ዩናይትዱ አጥቂ አሌክሲስ ሳንቼዝ አሁን በውሰት ባለበት ኢንተር ሚላን በቋሚነት መቆየት ከፈለገ ደሞዙን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ የግድ ይለዋል።
(Tuttosport via Daily Mail)
የኤቨርተኑ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የአሰልጣኝ ስታፉን ሰዎች እንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ነግሯቸዋል።
(Guardian)
በቡንደስ ሊጋው አስደናቂ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኘው ጄደን ሳንቾ በቼልሲ ፣ ማን ዩናይትድ እና ሊቨርፑል በጥብቅ ይፈለጋል።እንደ ጀርመኑ ጋዜጣ ቢልድ ዘገባ ከሆነ የ19 አመቱ እንግሊዛዊ የዝውውር ሒሳብ አሁን €140ሚ. ይገመታል።ሳንቾ በዘንድሮው አመት በሁሉም የውድድር አይነቶች በ33 ጨዋታዎች 17 ግቦችን ሲያስቆጥር 18 ኳስ ደግሞ ለግብ አመቻችቶ አቀብሏል።
(Bild)
ሮናልድ ኪውመን ባርሴሎና በአሰልጣኝነት ሊሾመው ጥያቄ አቅርቦለት ውድቅ ማድረጉን ተናገረ።በካታላኑ ክለብ በተጨዋችነት ስድስት አመታትን ያሳለፈው ኪውመን ከኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ስንብት በኋላ ባርሴሎና ለአሰልጣኝነት ጠይቆት እንደነበር ሆኖም እርሱ በሆላንድ ብሔራዊ ቡድን ለመቆየት መሻቱን ተናግሯል።
(Goal)
አትሌቲኮ ማድሪድ በባርሴሎና የመቆየት ዕድሉ አነስተኛ የሚመስለውን ክሮኤሽያዊውን አማካይ ኢቫን ራኪቲች ለማዘዋወር ይፈልጋል።ራኪቲች በስፔን መቆየትን ይሻል።
(Marca )
የስኮትላንዱ ክለብ ሬንጀርስ አሰልጣኝ የሆነው ስቴቨን ዤራርድ ከክለቡ የሚለቀው ክለቡ ካሰናበተው ብቻ እንደሆነ ተናግሯል።
(The Scotsman)
No comments:
Post a Comment