አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
(Goal)
ማንቸስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊውን አጥቂ ጄደን ሳንቾ ከማንቸስተር ዩናይትድ የማስፈረም ዕድሉ ከፍተኛ ነው።ቀያይ ሰይጣኖቹ ለ19 አመቱ ተጨዋች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የተጨዋቾች ዝውውር ሪከርድንም እንደሚሰብር ይጠበቃል።
(Telegraph)
ፈረንሳዊው አማካይ ፖል ፖግባ በዚህ ሳምንት ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ልምምድ የሚመለስ ሲሆን ብዙዎችም ድንቅ እንቅስቃሴን እያደረገ ካለው ከብሩኖ ፈርናንዴዝ ጋር የሚኖረውን ጥምረት በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ።
(ESPN)
የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ መድፈኞቹ በቀጣዩ አመት በሻምፒዮንስ ሊግ የመሳተፍ ዕድላቸው አናሳ መሆኑን ተከትሎ ፥ አዳዲስ ተጨዋቾችን ማግኘት አዳጋች እንዳይሆንበት እንደሚሰጋ ገልጿል።
(ESPN)
በቡንደስ ሊጋ አስደናቂ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘውን የአር.ቢ. ሌብሲሁን ጀርመናዊ አጥቂ ቲሞ ዋርነር ለማዘዋወር ሊቨርፑል እና ማን ዩናይትድ ፉክክር ውስጥ ገብተዋል ፥ የዝውውር ሂሳቡም £100ሚ. ገደማ እንደሚሆን ይጠበቃል።
(Express)
አትሌትኮ ቢልባኦ አርጀንቲናዊውን አጥቂ ጎንዛሎ ሂጎይን ከጁቬንትስ የማዘዋወር ፍላጎት አለው።ሂጎይን በላሊጋው ከዚህ ቀደም ለሪያል ማድሪድ መጫወቱ ይታወሳል።
(Marca)
በማንቸስተር ሲቲ በጥብቅ እየተፈለገ ያለው የኤቨርተኑ እንግሊዛዊ ተከላካይ ሜሰን ሆልጌት ስለ ዝውውር ዜናዎች ተጠይቆ ሙሉ ትኩረቱ ኤቨርተን ላይ እንደሆነ ተናግሯል።
(Mail)
ፍራንክ ላምፓርድ ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባልጋ በስታንፎርድ ብሪጅ እንደሚቆይ ተናገረ።
(Mail)
No comments:
Post a Comment