አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
አወዛጋቢው የናፖሊ ፕሬዝደንት ኦላሪዮ ደ ላውረንቲስ የኻሊዱ ኩሊባሊ መ'ሸጫ ዋጋ €99ሚ. እንዲሆን ወስነዋል።ሴኔጋላዊው ድንቅ ተከላካይ በበርካታ ሐያላን የአውሮፓ ክለቦች የሚፈለግ ሲሆን ከፈላጊዎቹ መሀከል ማንቸስተር ዩናይትድ ፣ ፒ.ኤስ.ጂ ፣ ባርሴሎና ፣ ሪያል ማድሪድ እና ማንቸስተር ሲቲ ይገኙበታል።
(Mail Online)
ፍራንክ ላምፓርድ ቋሚ ተሰላፊ እንደሚያደርገው ዋስትና ስላልሰጠው ፥ ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባልጋ በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ቼልሲን ለመልቀቅ ወስኗል።
(Mail)
የማንቸስተር ዩናይትዱ አለቃ ኦሌ ጉናር ሶልሻየር መልማዮችን ወደ ጣሊያን ልኳል።ሶልሻየር የላካቸው መልማዮች ተግባርም £60ሚ. የሚገመተውን የፍዮረንቲናውን የክንፍ አጥቂ ፌዴሪኮ ቼሳ በሜዳ ተገኝተው አቋሙን እንዲመለከቱ ነው።
(Mail)
የጀርመናዊው አማካይ ሜሱት ኦዚል ወኪል እንደተናገረው ከሆነ የ31 አመቱ ተጨዋች ውሉ እስኪጠናቀቅ ማለትም እስከ 2021 መድፈኞቹን ሳይለቅ በኤምሬትስ ይቆያል።
(inews)
የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አምበል ዴቪድ ቤካም ፖርቱጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ከአርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ እሱ በባለቤትነት በያዘው ኢንተር ሚያሚ ቢመጡ ደስተኛ እንደሚሆን ተናግሯል።
(ESPN)
መነሻው ቻይና የነበረው እና በአሁኑ ሰዓት በርካታ ሀገራት ላይ እየተስፋፋ የሚገኘው ኮሮና ቫይረስ በብዙ ሊጎች ላይ ስጋትን ደቅኗል።በዚህ ሳምንት ከግማሽ በላይ የጣሊያን ሴሪ ኤ ጨዋታዎች በዝግ ሜዳ የሚደረጉ ሲሆን ይህ ነገር ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግም ሊመጣ ይችላል።
(Telegraph)
ጁቬንትስ የማንቸስተር ሲቲውን ብራዚላዊ አጥቂ ጋብሬል ጄሱስ የማዘዋወር ፍላጎት አለው።የአሮጊቷ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ፋቢዮ ፓራቲቺ ከጓዶቻቸው ጋር የ22 አመቱን ተጨዋቾ ዕድገት ሲከታተሉ የሰነበቱ ሲሆን ክረምት ላይም ለማዘዋወር አቅደዋል።ጄሱስ በዘንድሮው አመት በሁሉም የውድድር አይነቶች በ36 ጨዋታዎች 18 ግቦችን ከመረብ አሳርፏል።
(Calcio Mercato)
አትሌቲኮ ማድሪድ የዊልያንን እና የቼልሲን ጉዳይ በአጽንኦት በመመልከት ላይ ይገኛል።ዲያጎ ሲሞኑ ብራዚላዊው አጥቂ በቼልሲ ውሉን ካላራዘመ በነጻ ዝውውር ወደ ዋንዳ ሜትራ ፖሊታኖ እንዲመጣለት ይሻል።ባርሴሎና እና ቶተንሃምም የዊልያን ፈላጊዎች ናቸው።
(Tuttomercatoweb)
ስመ ጥሩ ጋዜጣ ፎር ፎት ቱ ከሰሞኑ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ የታዩ ምርጥ 100 ተጨዋቾችን በአያሌ መመዘኛዎች መዝኖ ይፋ አድርጓል።እኛም ከ1-20 ያሉትን እንደሚከተለው አሰናድተናል።
20.ፒተር ሽማይክል
19.ቨንሶ ኮምፓኒ
18.ዴኒስ ቤርካምፕ
17.ፔትር ቼክ
16.ሙሐመድ ሳላህ
15.ሰርጂዮ አጉዌሮ
14.አሽሊ ኮል
13.ሪዮ ፈርዲናንድ
12.ጆን ቴይሪ
11.ሪያን ጊግስ
10.ፓትሪክ ቬይራ
9.ሮይ ኪን
8.ስቴቨር ዤራርድ
7.ፖል ስኮልስ
6.ፍራንክ ላምፓርድ
5.ኤሪክ ካንቶና
4.ዌይን ሩኒ
3.አሌን ሽረር
2.ክርስቲያኖ ሮናልዶ
1.ቴይሪ ሄንሪ
ምንጭ - Four Four Two
No comments:
Post a Comment