Thursday, March 5, 2020

የዕለተ አርብ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች

               አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ኦሌ ጉናር ሶልሻየር በአዲሱ ፈራሚው ኦዲዮን ኤግሃሎ አቋም መደሰቱን ተናገረ።ትናንት በኤፍ.ኤ.ካፕ አምስተኛ ዙር ማንቸስተር ዩናይትድ ደርቢ ካውንቲን በረታበት ጨዋታ ናይጄሪያዊው አጥቂ ሁለት ግብ ማስቆጠር ችሏል።ኤግሃሎ ከቻይናው ክለብ ሻንጋይ ሺኖዋ ቀያይ ሰይጣኖቹን በውሰት ከተቀላቀለ አንስቶ በስድስት ጨዋታዎች ሶስት ግብ ከመረብ አሳርፏል።
(Goal)





ጁቬንትስ ማውሮ ኢካርዲን ለማዘዋወር በክረምቱ የዝውውር መስኮት ዳግም ጥረት ያደርጋል።አሮጊቷ አርጀንቲናዊውን አጥቂ በተደጋጋሚ ለማዘዋወር ጥረት ማድረጓ የሚታወስ ሲሆን አሁን ግን ትልሟን ከግብ ለማድረስ €100ሚ. ለፓሪሰን ዤርመን መክፈል ይጠበቅባታል።
(Calciomercato)





ማንቸስተር ሲቲ የተከላካይ ስፍራውን ለማጠናከር የኢንተር ሚላኑን ድንቅ ተከላካይ ሚላን ስክሪኒያር ማዘዋወር ይፈልጋል።ኢንተር ሚላን የ25 አመቱን ስሎቫኪያዊ በክለቡ ማቆየት የሚሻ ሲሆን €85ሚ. ከቀረበለት ግን ሀሳቡን ይቀይራል።
(Calciomercato)





አርሰናል የፌይኖርዱን ታዳጊ ኦርኩን ኮኩ ለማዘዋወር ሶስት ተጨዋቾችን ለመሸጥ ወስኗል።እነዚህ ሶስት ተጨዋቾች ሜሱት ኦዚል ፣ ማቲዮ ጊውንዶዚ እና ሶቅራጠስ ፓፓስታፓውሎስ ናቸው።
(The Daily Mail)





ሮማ እንግሊዛዊውን ተከላካይ ክሪስ ስሞሊንግ በቋሚነት በክለቡ ለማቆየት €25ሚ. ለማንቸስተር ዩናይትድ መክፈል ይጠበቅበታል።ስሞሊን በውሰት የጣሊያኑን ክለብ ከተቀላቀለ አንስቶ ድንቅ እንቅስቃሴን በማድረግ ላይ ይገኛል።
(Metro)





ፖል ፖግባ በማንቸስተር ዩናይትድ ሊቆይ ይችላል።ምንም እንኳን የፈረንሳዩ አማካይ ስም በስፋት ከሪያል ማድሪድ እና ጁቬንትስ በኦልድ ትራፎርድ የሚቆይበት ዕድልም አለ።የብሩኖ ፈርናንዴዝ መምጣት ደግሞ ምክንያት ሊሆን ይችላል።
(Daily Star)




የኤርሊንግ ሀላንድ አባት ልጃቸው ስፔን ላሊጋ ላይ ቢጫወት ደስተኛ እንደሚሆኑ ተናገሩ። "የልጄ ስም ከመቶ በላይ ቡድኖች ጋር ሲያያዝ ቆይቷል።ነገር ግን ስፓኒሽ ላሊጋ ለልጄ ጥሩ ሊግ ይመስለኛል ፥ ታላላቅ ክለቦችም ይገኙበታል" ነው ያሉት።ይህንንም ተከትሎ የሀላንድ ስም በስፋት ከሪያል ማድሪድ ጋር እየተያያዘ ይገኛል።
(Goal)






የቀድሞው የእግር ኳስ ኮከብ ሮናልዲንሆ ጎቾ በፓራጓይ መታሰሩ ይፋ ሆኗል።ብራዚላዊው የቀድሞው ኮከብ በፓራጓይ ህገ-ወጥ የፓራጓይ  ፓስፖርት ይዞ ነው የተገኘው።ፓስፖርቱ ላይ ሮናልዲንሆ ዜግነቱ ፓራጓዊ እንደሆነ ይጠቅስ እንደነበርም ታውቋል።
(La Nacion)





የ26 አመቱ እንግሊዛዊ አጥቂ ሀሪ ኬን በቶተንሃም አዲስ ውል የመፈረም ፍላጎት የለውም።ኬን ማንቸስተር ዩናይትድ የሚፈልገው ከሆነ ቀያይ ሰይጣኖቹን የመቀላቀል ፍላጎትም አለው።
(Goal)


No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...