Saturday, March 7, 2020

ቅድመ ጨዋታ ትንታኔ | ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ማንቸስተር ሲቲ

ቅድመ ጨዋታ ትንታኔ | ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ማንቸስተር ሲቲ

        አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)




ዛሬ ምሽት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለቱ የማንቸስተር ከተማ ክለቦች በኦልድ ትራፎርድ ይገናኛሉ።ምንም እንኳን ሁለቱም ክለቦች በዚህ ዓመት የሊጉን ዋንጫ የመቀዳጀት ዕድላቸው ግመልን በመርፌ ቀዳዳ የማሾለክ ያህል ቢሆንም የደርቢው ታላቅነት ግን ጨዋታውን በጉጉት እንዲጠበቅ ያደርገዋል።

ባለ ሜዳው ማንቸስተር ዩናይትድ ከብሩኖ ፈርናንዴዝ መመጣት በኋላ ስኬታማ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኝ ሲሆን በዛሬውም ጨዋታ የፖርቱጋላዊው ሚና ከፍተኛ እንደሚሆን ይገመታል።

የፔፕ ጋርዲዮላው ማንቸስተር ሲቲም ከሻምፒዮንስ ሊጉ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት መታገዱን በሰማ ማግስት ሪያል ማድሪድን ሳንቲያጎ በርናቢዮ ላይ በመርታት መነቃቃት ላይ ይገኛል።


የቡድን ዜናዎች



➡️በሁለቱም ቡድኖች መሀከል ቁልፍ ተጨዋቾች ለዛሬው ጨዋታ መድረሳቸው አጠራጣሪ ነው።ከማንቸስተር ሲቲ ኬቨን ደ ብሮይነ ከማንቸስተር ዩናይትድ ደግሞ ሀሪ ማጉዌር።

➡️ደ ብሮይነ ጉዳት ላይ በመሆኑ በኤፍ.ኤ.ካፕ ሲቲ ከ ሄልስ ቦሮ ጋር ከነበረው  ጨዋታ ውጪ መሆኑ ይታወሳል።ፔፕ ጋርዲዮላ በቅድመ ጨዋታ ቃለ መጠይቁ ላይ "አሁን ደህና ነው" ያለ ቢሆንም ለዛሬ መድረሱ አልረጋገጠም።


➡️በሲቲ በኩል አይምሪክ ላፖርቴ እና ለሮይ ሳኔ ከጨዋታው ውጪ ናቸው።

➡️ማርከስ ራሽፎርድ እና ፖል ፖግባ ከዛሬው ጨዋታ ውጪ ናቸው።

➡️ብሩኖ ፈርናንዴዝ የመሀል ሜዳውን እንደሚመራው የሚጠበቅ ሲሆን ኦዲዮን ኤግሃሎም ዛሬ ሊሰለፍ ይችላል።



የእርስ በርስ ግንኙነት


ማንቸስተር ሲቲ በሁሉም የውድድር አይነቶች ዩናይትድን ኦልድ ትራፎርድ ላይ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች መርታት ችሏል።ዛሬ የሚያሸንፍ ከሆነ ለአራተኛ ጊዜ ይሆናል።ይህ የሚሆን ከሆን ከ1931 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።


በዚህ ደርቢ ካለፉት ስምንት ጨዋታዎች ባለ ሜዳው ማሸነፍ የቻለው አንዱን ብቻ ነው።አንድ አቻ ሲሆን ስድስቱ ከሜዳ ውጪ የተመዘገቡ ድሎች ናቸው።

ዩናይትድ ዛሬ ካሸነፈ  በአስር አመት ውስጥ Back to back ሲያሸንፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሆናል።



ግምታዊ አሰላለፍ



ማን ዩናይትድ
ዴሄያ | ዋን ቢሳካ | ሊንደሎፍ | ማጉዌር | ሾው | ማቲች | ፍሬድ | ጄምስ | ፈርናንዴዝ | ማርሺያል | ኤግሃሎ

ማን ሲቲ
ኤደርሰን | ዎከር | ኦታሜንዲ | ፈርናንዲንሆ | ሜንዲ | ደ ብሮይነ | ሮድሪ | ጉንዶጋን | ማህሬዝ | አጉዌሮ | ስተርሊንግ


No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...