አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ሰሞኑን የሊዮኔል ሜሲ ስም ከዝውውር ጋር በሰፊው በመያያዝ ላይ ይገኛል።ኤክስፕረስ ዛሬ እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ የ32 አመቱ አርጀንቲናዊ በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ወደ ማንቸስተር ሲቲ እንዲመጣ ውሃ ሰማያዊዎቹ ይፈልጋሉ።
(Express)
ጉዳት ላይ የሰነበተው የማንቸስተር ሲቲው አጥቂ ራሂም ስተርሊንግ ክለቡ በሻምፒዮንስ ሊግ ከሪያል ማድሪድ ጋር ላለበት ጨዋታ እንደሚመለስ ይጠበቃል።
(Telegraph)
የቀድሞው የቶተንሃም አሰልጣኝ ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆ በዚህ አመት የትኛውንም ክለብ ለማሰልጠን ያልወሰነው በቀጣዩ ማንቸስተር ዩናይትድን ስለሚይዝ ነው ሲል ሚረር አስነብቧል።
(Mirror)
ባለቤትነቱ የባርሴሎና ሆኖ በውሰት ባየርን ሙኒክ የሚገኘው ብራዚላዊው አማካይ ፌሊፔ ኩቲንሆ በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ማረፊያው ማንቸስተር ሲቲ ወይም የቀድሞው ክለቡ ሊቨርፑል እንደሚሆን ይጠበቃል።
(Express)
ስሙ ከባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ ጋር በስፋት ሲያያዝ የነበረው ቤልጄሚያዊው የማንቸስተር ሲቲ አማካይ ኬቨን ደ ብሮይነ አሁን በኢቲሀድ ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል።
(Goal)
በሪያል ማድሪድ አመታትን ያሳለፈው ዌልሳዊው ኢንተርናሽናል ጋሬዝ ቤል ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር በተለይም ከቶተንሃም ጋር ቢያያዝም እርሱ ግን ወደ ቻይና የመሄድ ዕድሉ ሰፊ እንደሆነ እየተዘገበ ይገኛል።
(Goal)
በዝውውር መስኮት ስሙ ከማንቸስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ ጋር ሲያያዝ የነበረው ኡራጋዊያዊው የፓሪሰን ዤርመን አጥቂ ኤዲንሰን ካቫኒ በአመቱ መጨረሻ በፓርክ ደ ፕሪንስ ያለው ኮንትራት ሲያበቃ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መሄዱ አይቀሬ ነው።
(L'Equipe, via Star)
ከአርሰናል ጁቬንትስን ተቀላቅሎ በቱሪን የተጨዋች ህይወቱን እየገፋ የሚገኘው ዌልሳዊው ኢንተርናሽናል አሮን ራምሴ ከጣሊያን መውጣትን ይሻል።
(Calciomercato - in Italian)
ሊቨርፑል በቀጣዩ የዝውውር መስኮት አንድ የግራ መስመር ተከላካይ እና ጀርመናዊውን የራ.ቢ ሌብዝሽ አጥቂ ቲሞ ዋርነር ማዘዋወር ይፈልጋል።
(Athletic, via Team Talk)
No comments:
Post a Comment