አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ማንችስተር ሲቲዎች በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ሊዮኔል ሜሲን ማስፈረም እንደሚፈልጉ ዘ ኤክስፕረስ ዛሬ አስነብቧል ዝውውሩ የመሳካት እድል ባይኖረውም ሲቲዎች ግን ፍላጎት አላቸው።
ዩናይትድ እና አስቶንቪላ በጃክ ግሪሊሽ ዝውውር ጉዳይ ተቀምጠው ለመነጋገር ቀጠሮ ይዘዋል ዛሬ በርካታ የእንግሊዝ ጋዜጦች ዩናይትድ ክረምት ላይ ተጨዋቹን እንደሚያስፈርሙት በእርግጠኝነት እየዘገቡ ይገኛሉ።
አርሰናሎች የቀድሞ አሰልጣኛቸውን አርሰን ዌንገርን በሌላ የስራ ሚና ወደ ኢምሬት ለመመለስ እየሰሩ ነው የክለቡ ሰዎች ዌንገርን ለማስማማት ንግግጌ ላይ ናቸው።
በዘንድሮ ሲዝን አርሰናልን ለቆ ወደ ጣሊያኑ ጁቬንቱስ በነፃ የተዘዋወረው አሮን ራምሴ በአሮጊቶቹ ቤት ብዙም የመሰለፍ እድልን እያገኘ አደለም ይህንን ተከትሎ ራምሴ በክረምቱ የዝውውር መስኮን ጁቬን መልቀቅ ይፈልጋል።
ሊቨርፑሎች በግራ ተከላካይ መስመር ያለባቸውን የተጠባባቂ ተጨዋች ችግርን ለመቅረፍ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የግራ መስመር ተከላካይ እንደሚያስርሙ ታውቋል።
ባሳለፍነው ክረምት ማንችስተር ዩናይትድ አልያም ቶተንሀም ሊገባ ነው ሲባል የሰነበተው አርጀንቲናዊው ፓብሎ ዲባላ በቱሪን ለተጨማሪ አመት ለመቆየት ወስኗል በጁቬም አዲስ ኮንትራት ለመፈረም ከጫፍ ደርሷል.
ማውሪሲዮ ፖቸቲንሆ አሁንም ፍላጎቱ ዩናይትድ እንደሆነ ሚረር አስነብቧል ከቶተንሀም ከተሰናበተ ቡሀላ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ ቢሰነብትም እሱ የሱ ምርጫ ግን አሁንም ዩናይትድ ነው።
የፒኤስጂ ዋና አለቃ ናስር አልካላፊ በምንም አይነት መልኩ በክረምት ክሊያን ምባቤን ለመልቀቅ ለድርድር እንደማይቀመጡ ሲናገሩ በተጨማሪም ተጨዋቹን ተጨማሪ ኮንትራት ለማስፈረም እየሰሩ መሆኑን ይፋ አርገዋል።
No comments:
Post a Comment