አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ባየርን ሙኒክ ብራዚላዊውን የሊቨርፑል አጥቂ ሮበርቶ ፈርሚንሆ ለማዘዋወር £75ሚ. የመደበ ሲሆን የባቫሪያው ክለብ የማንቸስተር ሲቲውን ለሮይ ሳኔንም ማዘዋወር ይሻል።
(Sun)
በማንቸስተር ዩናይትድ የአንድ አመት ኮንትራት የቀረው ፈረንሳዊው ኢንተርናሽናል ፖል ፖግባ በመጪው ክረምት ከቲያትር ኦፍ ድሪምስ ለመውጣት አቅዷል።የ26 አመቱ ኮከብ በዚህ አመት በጉዳት ምክንያት በርካታ ጨዋታዎች ላይ አለመሰለፉ ይታወቃል።
(Manchester Evening News)
ማንቸስተር ዩናይትድ በጥብቅ ሲፈልገው የነበረው እንግሊዛዊው የሌስተር ሲቲ አማካይ ጄምስ ማዲሰን በቀበሮዎቹ ቤት አዲስ ኮንትራት ሊፈርም ነው።
(Express)
የርገን ክሎፕ የቡድናቸውን ስኳድ ይበልጥ ለማጠናከር በቀጣዩ የውድድር መስኮት ጀርመናዊውን የባየርን ሊቨርኩሰን አማካይ ካይ ሀቨርትዝ ማዘዋወር ይፈልጋሉ።
(Express)
በተለይ በማንቸስተር ዩናይትድ በጥብቅ የሚፈለገው ሴኔጋላዊው የናፖሊ ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ በዝውውር ሒሳቡ £128ሚ. መሆኑን ሚረር ገልጿል።
(Mirror)
ጣሊያናዊው የቼልሲ አማካይ ጆርጊንሆ ከቀድሞው አሰልጣኙ ማውሩዚዮ ሳሪ ጋር በጁቬንትስ ለመስራት ፍላጎት እንዳለ'ው ወኪሉ ተናግሯል።
(Mail)
ካሜሮናዊው የአያክስ ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና በፓሪሰን ዤርመን እና ባርሴሎና የሚፈለግ ቢሆንም የእርሱ ምርጫ ግን የእንግሊዙ ክለብ ቼልሲ ነው።
(Caught Offside)
ክሎፕ በውሰት ባየርን ሙኒክ የሚገኘውን የባርሴሎናውን ብራዚላዊ አማካይ ፌሊፔ ኩቲንሆ ወደ ሊቨርፑል መመለስ ይፈልጋሉ።
(Star)
No comments:
Post a Comment