Monday, February 10, 2020

የዕለተ ሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ



                            


ባየርን ሙኒኮች ፊሊፔ ኩቲትሆን እንዲሁም ሊዩሬ ሳኔን ማስፈረም ይፈልጋሉ።እንደ  ዘገባዎች ከሆነ ሙኒኮች ለኩቲንሆ እስከ £75m መድበዋል ሊቨርፑሎችም ከአሁኑ ስጋት ውስጥ ገብተዋል ።




በዚህሳምንት ጉዳት ላይ የነበሩት በጨዋቾች ወደ ልምምድ እየተመለሱ ይገኛሉ. ከጥር መጀመሪያ  ጀምሮ ለዩናይትድ ግልጋሎት ያልሰጠው ስኮት ማክቶሚናይ ወደ ልምምድ ተመልሷል። እንዲሁም የሊቨርፑሉ ሳዲዮ ማኔም ወደ ልምምድ ተመልሷል።




በበርካታ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች የሚፈለገው ሴኔጋላዊው የናፖሊ ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ በክረምቱ ወደ ዩናይትድ የማምራት እድሉ ሰፊ ነው።




ጁቬዎቹ በክረምቱ ፖል ፖግባን ለማስፈረም ቀዳሚ ምርጫቸው አድርገውታል።እንደ ካልቺዮ መርካቶ ዘገባ ከሆነ ጁቬዎች በክረምቱ ትልልቅ ዝውውር ለመፈፀም ዝግጅት ላይ ሲሆኑ ተጨዋቹም ፖግባ ሆኗል።




ከጊዜወደጊዜ መሻሻሎችን እያሳየ የሪያል ማድሪዱ ቲቦቱ ኮርቱዋ የስፔን ላሊጋ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ሆኗል።




ሊቨርፑሎች በክረምቱ የዝውውር መስኮት የመሀል አማካይ ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው። ከአሁኑም ስማቸው ከተለያዩ ተጨዋቾች ጋር እየተነሳ ይገኛል። የክሎፕ ተቀዳሚ ምርጫ ግን የባየርን ሌቨርኩለኑ ካይ ሀቨርትስ ነው። በተጨማሪም ሊቨርፑሎች የቀድሞ ኮከባቸውን ከቲትሆንም መመለስ ይፈልጋሉ።




ካሜሮናዊው የአያክስ ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና የመጀመሪያ ምርጫው ቸልሲ ሆኗል።በተለያዩ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች ባርሴሎና እና ፒኤስጂ ቢፈለግም ተጨዋቹ ግን በላምፓርድ እምነት ያጣውን አሪዛባላጋን በመተካት ብሪጅ መድረስ ነው ሚፈልገው።



በዚህ ሳምንት የእንግሊዝ ክለቦች እረፍት መሆናቸው ይታወሳል።ይህንንም ተከትሎ ጆዜ ትናንት በአሊያንዝ አሬና በመገኘት የአርቢ ሌብዢክን ጨዋታ ተመልክተዋል።ቶተንሀሞች በቀጣይ ሳምንት በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ሌብዢክን ይገጥማል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...