Monday, February 10, 2020

የዕለተ ማክሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)



ጁቬንትስ የማንቸስተር ሲቲውን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በዋና አሰልጣኝነት ለመሾም ፍላጎት አላት።አሮጊቷ ለ49 አመቱ ስፓኒያርድ ከፍተኛ ደሞዝ እና ጥሩ ፕሮጀክትም አሰናድታለታለች።
(Sun)





ባርሴሎና ብራዚላዊውን የ27 አመት አማካይ ፌሊፔ ኩቲንሆ በቀጣዩ የዝውውር መስኮት እንደሚለቀው ይጠበቃል።ኩቲንሆ በማንቸስተር ዩናይትድ ፣ ቼልሲ ፣ ማንቸስተር ሲቲ ፣ ቶተንሃም እና በቀድሞው ክለቡ ሊቨርፑል ይፈለጋል።
(Express)





ማንቸስተር ሲቲ ኖርዌያዊውን የቦሩሲያ ዶርትሙንድ አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ የረዥም ጊዜ የሰርጂዮ አጉዌሮ ተተኪ ማድረግ ይሻል።ሀላንድ በዚህ ሲዝን ድንቅ እንቅስቃሴን በማድረግ ብዙሃኑን የእግር ኳስ አፍቃሪ አጀብ ያሰኘ አጥቂ ነው።
(90min.com)





የቶተንሃሙ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ በቀጣዩ የዝውውር መስኮት የበርንማውዙን ተከላካይ ናታን አ'ኬ እና የቤኔፊካውን ተከላካይ ሩበን ዲያዝ ለማዘዋወር አቅደዋል።
(Express)





ማንቸስተር ዩናይትድ በውሰት ለኢንተር ሚላን የሰጠውን የ31 አመቱን ቺሊያዊ አጥቂ አሌክሲስ ሳንቼዝ ለመሸጥ ፍላጎት ያለው ሲሆን ገዢዎችን በማፈላለግ ላይ ይገኛል።
(Manchester Evening News)





የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ክለቡ አሁን እስከ አራተኛ ደረጃ ይዞ የማጠናቀቅ ዕድሉ አዳጋች ሊሆን እንደሚችል ተናግሯል።መድፈኞቹ አራተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው የከተማ ተቀናቃኛቸው ቼልሲ በአስር ነጥብ ያንሳሉ።
(Evening Standard)





ማንቸስተር ዩናይትድ ለ2020-21 ቅድመ ዝግጅት አዲስ ዕቅድ ለማውጣት እየተሰናዳ ነው።የዚህ ምክንያት ደግሞ መጀመሪያ ዕቅዳቸው ቻይና ስለነበር እና አሁን በቻይና ኮሮና ቫይረስ በመከሰቱ ሳቢያ ነው ተብሏል።
(ESPN)






አሁን በኢንተር ሚላን የሚገኘው የቀድሞው የቶተንሃም አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን በተጨዋችነት ህይወቱ እንደ ሚላን ደርቢ አይነት ድንቅ ድባብ አይቶ እንደማያውቅ ተናግሯል።
(Goal)





No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...