Tuesday, February 11, 2020

የዕለተ ማክሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

                     አዘጋጅ- ኢብራሒም ሙሐመድ


ማንችስተር ሲቲዎች ኤርሊንግ ሀላንድን የሰርጂዮ አጉዌሮ የረጅም ጊዜ ተተኪ ለማድረግ ፍላጎት አላቸው። ሲቲዎች ለአጉዌሮ የወደፊቱ እጣ ፋንታው በእጁ ላይ እንዳለ ነግረውታል በኢትሀድ መቆየት ወይም ከኢትሀድ መልቀቅ።





በጥርየ ዝውውር መስኮት ወደ ኤሲ ሚላን ለማምራት ከጫፍ ደርሶ የነበረውን የዊጋን አትሌቲኩ የግራ መስመር ተጨዋች አንቶኒ ሮቢንሰን በሶስቱ የእንግሊዝ ክለቦች ቸልሲ፣ ኒውካስትል እና አስቶንቪላ የዝውውር ራዳር ውስጥ ገብቷል።




በተለያየ ጊዜ በትላልቅ ክለቦች ራዳር ውስጥ ሚገባው የዋትፎርዱ አብዱላሂ ዶኮሬ በቀጣይ አመት በቻምፒየንስ ሊግ ለሚጫወት ክለብ መጫወት እንደሚፈልግ ተናገረ። በክረምትም ዋትፎርዶች እንዲለቁት ጥያቄ አቅርቦላቸዋል።





ታላላቆቹ የእንግሊዝ ክለቦች ፖርቱጋላዊውን ተከላካይ ሩበን ዲያዝን ለማስፈረም ተፋጠዋል። በተለይም በተደጋጋሚ ስማቸው ከልጁ ጋር ሚነሳው ዩናይትዶች ባሳለፍነው ሳምንት መልማዮችን ልከው ልጁን መመልከታቸው ታውቋል። ከዩናይትድ በተጨማሪም ማን ሲቲ ቶተንሀም ሊቨርፑል የልጁ ዋና ፈላጊዎች ናቸው።





በማውሪዚዮ ሳሪ ደስተኛ ያልሆኑት ጁቬንቱሶች ኢላማቸውን ስፔናዊውን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላን አርገዋል። ጁቬዎች ጋርዲዮላን ዘንድሮ ባያገኙትም ሲቲን በሚለቅ ሰአት ለመቅጠር ዝግጁ ሆነዋል።




ቸልሲዎች ለሀርት ፑል የሚጫወተውን የ17 አመቱን ግብ ጠባቂ ብራድ ያንግን ለማስፈረም ከዩናይትድ እና ከአርሰናል የተሻለ እድል እንዳላቸው ተሰምቷል።





ዩሊያንት ብራንት በጉዳት ምክንያት ለአንድ ወር ቦሩሲያ ዶርትመንድን እንደማያገለግል ተረጋግጧል። በዚህም ዶርትመንዶች በቻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ፒኤስጂን ሲገጥሙ በሁለቱም ጨዋታዎች የብራንትን ግልጋሎት አያገኙም።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...