Tuesday, February 11, 2020

የዕለተ ረቡዕ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                  አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ማንቸስተር ዩናይትድ በቼልሲ በጥብቅ የሚፈለገውን እንግሊዛዊውን የቦሩሲያ ዶርትሙንድ አጥቂ ጄደን ሳንቾ ለማዘዋወር £120ሚ. አሰናድቷል።
(Mirror)





ሊቨርፑል ለኔዘርላንዳዊው ተከላካይ ቨርጅል ቫን ዳይክ አዲስ ኮንትራት ሊያቀርብለት ነው።በአዲሱ ኮንትራት መሰረት የ28 አመቱ ተከላካይ በሳምንት ከ£150,000 በላይ እንደሚከፈለውም ይጠበቃል።
(Football Insider)





ማንቸስተር ዩናይትድ በቀጣዩ ክረምት የሊዮኑን የ23 አመት ፈረንሳዊ አጥቂ ሙሳ ዴምቤሌ ለማዘዋወር ጥረት ያደርጋል።
(L'Equipe, via Manchester Evening News)




ቶተንሃም ሆላንዳዊውን የበርንማውዝ ተከላካይ ናታን አኬ ለማዘዋወር £40ሚ. አሰናድቷል።ጆዜ ሞሪንሆ የተከላካይ ስፍራቸውን ማጠናከር አጥብቀው ይሻሉ።
(Express)





ቤልጄሚያዊው የናፖሊ አጥቂ ድረስ መርቲንስ በአመቱ መጨረሻ በኔፕልስ ያለው ኮንትራት የሚያበቃ ሲሆን ቼልሲ ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ እና አርሰናል ደግሞ ፈላጊዎቹ ናቸው።
(Mail)





ቼልሲ በጥር ወሩ የዝውውር መስኮት ሁለት ጊዜ ሊያዘዋወር ሞክሮ ያልተሳካለትን የአያክሱን ሞሮኮዋዊ የክንፍ አጥቂ ሀኪም ዚያች  ለማዘዋወር አሁንም በመስራት ላይ ይገኛል።
(Telegraph)





ክረምት ላይ በቶተንሃም ያለው ኮንትራት የሚያበቃውን ቤልጄሚያዊውን ተከላካይ ያን ቨርቶገን ለማዘዋወር አያክስ ፍላጎት አለው።
(Guardian)





ማንቸስተር ሲቲ ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ ፣ ሊቨርፑል እና አትሌቲኮ ማድሪድ የቬሮናውን አልባኒያዊ ተከላካይ ማራሽ ኩምቡላ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።
(Gazzetta dello Sport, via Sport Witness)






No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...